የክሊንተን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት | ዓለም | DW | 04.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የክሊንተን የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት

የዩናይይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ኪንተን ስልጣን ከያዙ ወዲህ የመጀመሪያው በሆነው የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝታቸው ዛሬ ራማላህ ውስጥ ከፍልስጤም መሪዎች ጋር ተነጋገሩ ።

default

ክሊንተን እና አባስ

ክሊንተን የፍልስጤም መስተዳደር መሪዎችን ባነጋገሩበት ወቅትም በእስራኤሉ ጉብኛቸው እንዳሉት ሁሉ አዲሱ የባራክ ኦባማ አስተዳደር እስራኤልና ፍስልጤማውያን ጎን ለጎን በሰላም እንዲኖሩ የተቻለውን ሁሉ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ። ክሊንተን ትናንት እስራኤል ውስጥ በሰጡት መግለጫ ደግሞ መንግስታቸው በአካባቢው ሁሉን አቀፍ የሰላም ዕቅድ ለማራመድ መነሳቱን አስታውቀው የእስራኤል ባላንጣ ወደ ሆነችው ወደ ሶሪያም መልዕክተኞችን እንደሚልኩም ይፋ አድርገዋል ።