የኬንያ ፖሊስ 23 ኢትዮጵያዉያንን ከጥቃት አዳነ | አፍሪቃ | DW | 10.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኬንያ ፖሊስ 23 ኢትዮጵያዉያንን ከጥቃት አዳነ

የኬንያ ፖሊስ በተቆጡ ኬንያዉያን የተከበቡ 23 ኢትዮጵያዉያንን ከኃይል ጥቃት ማዳኑ ተዘገበ። በአንድ የተፋፈገ መኖርያ ቤት ተደብቀዉ የተገኙት ኢትዮጵያዉያን ባሉበት አካባቢ ወንጀል መፈፀሙ ካስቆጣቸዉ ኬንያዉያን ዓይን ዉስጥ የገቡት በድንገት ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:09
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:09 ደቂቃ

የኬንያ ፖሊስ ኢትዮጵያዉያንን ማዳኑ

ፖሊስ እነዚህን ኢትዮጵያዉያን ሕገ-ወጥ ስደተኞች ያዳነዉ ልዩ የመከላከያ ኃይል ጠርቶና ወደ ሰማይ ተኩሶ መሆኑ ተመልክቶአል። በአሁኑ ወቅት እስር ቤት እንደሚገኙ የተነገረዉ እነዚህ ኢትዮጵያዉያን አብዛኞቹ ምንም ዓይነት መታወቂያ የሌላቸዉ ናቸዉ። ኪስዋሂሊም ሆነ እንጊሊዘኛ ቋንቋ አለመናገራቸዉ ነገሩ ን እንዳከበደባቸዉም ፖሊስ ተናግሮአል። ስለ ሁኔታዉ ኬንያ ናይሮቢ የሚገኘዉን ወኪላችንን በስልክ ጠይቄዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic