የኬንያ ፖሊስ ዘመቻና ኢትዮጵያዉያን የኦሮሞ ስደተኞች | ኢትዮጵያ | DW | 23.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኬንያ ፖሊስ ዘመቻና ኢትዮጵያዉያን የኦሮሞ ስደተኞች

የኬንያ ምክር ቤት ባለፈዉ ጥቅምት ባፀደቀዉ ሕግ ኦነግን ከተደራጀ የወንጀለኞች ቡድን ፈርጆታል

default

ናይሮቢ

የኬንያ ፖሊስ በሐገሪቱ የሠፈሩ የኢትዮጵያ የኦሮሞ ስደተኞች ከሌሎች ነጥሎ በመዘመቻ እያሰሰ ማሰሩን ስደተኞቹና የስደተኞቹ ማሕበር አስታወቁ።የስደተኞቹ ማሕበር ተጠሪዎች እንደሚሉት ፖሊስ የኦሮሞ ተወላጆችን ሁሉ የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ድርጅት (ኦነግ) አባላት ናችሁ እያለ በርካታ ስደተኞችን አስሯል።ሌሎቹንም ለማሳር አሰሳዉን ቀጥሏል።የኬንያ ምክር ቤት ባለፈዉ ጥቅምት ባፀደቀዉ ሕግ ኦነግን ከተደራጀ የወንጀለኞች ቡድን ፈርጆታል።የኦነግ ባለሥልጣናት የኬንያን መንግሥት እርምጃ አዉግዘዉታል።የናይሮቢዉ ወኪላችን ዘርይሁን ተስፋዬ ጉዳዩን ተከታትሎታል።

ዘርይሁን ተስፋዬ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ