የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መግለጫ   | አፍሪቃ | DW | 20.09.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

 የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መግለጫ  

ተቃዋሚዎች ነፃ የሚባለው የኬንያ የምርጫ እና የድንበር ኮሚሽን ኮምፕዩተር ተጠልፏል የሚል ክስ ካቀረቡ በኋላ ኮሚሽኑ ኮምፕዩተሩን ክፍት እንዲያደርግ የተሰጠውን ትዕዛዝ ሳያከብር መቅረቱን የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ አስታውቀዋል። እንደ ፍርድ ቤቱ ኮሚሽኑ የሚደብቀው ነገር ባይኖር ኖሮ ኮምፕዩተሩን ክፍት ያደርግ ነበር ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:21
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:21 ደቂቃ

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ዝርዝር መግለጫ

የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ባለፈው ነሐሴ 2፣2009 ዓም የተካሄደው የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ለመሰረዙ ተጠያቂው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ነው ሲል  አስታወቀ። ዛሬ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ሙሉ ውሳኔ በዝርዝር ያሳወቁት ምክትል ዋና ዳኛ ፊሎሜና ሙዊሉ፣ ተቃዋሚዎች ነፃ የሚባለው የኬንያ የምርጫ እና የድንበር ኮሚሽን ኮምፕዩተር ተጠልፏል የሚል ክስ ካቀረቡ በኋላ ኮሚሽኑ ኮምፕዩተሩን  ክፍት እንዲያደርግ የተሰጠውን ትዕዛዝ ሳያከብር መቅረቱን አስታውቀዋል።  ሙዊሊ እንዳሉት ኮሚሽኑ የሚደብቀው ነገር ባይኖር ኖሮ ኮምፕዩተሩን ክፍት ያደርግ ነበር ። ራይላ ኦዲንጋ የሚመሩት የተቃዋሚዎቹ ፓርቲ «ብሔራዊ ላአላይ ህብረት» በምህጻሩ «ናሳ» ጠበቆች የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ድጋሚ ተመረጡ የተባለበት ምርጫ ተጭበርብሯል፣ ሒደቱ ተጽዕኖ ተደርጎበታል ድምጾችም ተጠልፈዋል ሲሉ ከሰው ነበር።  የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዋጋ ቢስ፤ ተቀባይነት የሌለዉ እና ዉቅድ ነው ሲል የወሰነው ነሐሴ 26፣2009 ዓም ነበር። ፍርድ ቤቱ ዛሬ ሥለሰጠው ዝርዝር መግለጫ እና የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሑሩ ኬንያታ እና የተቃዋሚዎቹ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ዛሬ ተገናኝተው ይወያያሉ ስለመባሉ ናይሮቢ የሚገኙትን የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ፍቅረ ማርያም መኮንን በስልክ አነጋግሬያቸዋል። አቶ ፍቅረ ማርያም ለዛሬ ታቅዶ ስለ ነበረው የኬንያታ እና የኦዲንጋ ውይይት በማብራራት ይጀምራሉ።

ኂሩት መለሰ 
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች