የኬንያ ባለስልጣናት እና ICC | ዓለም | DW | 06.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኬንያ ባለስልጣናት እና ICC

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ትናንት በምክትል ፕሬዝደንቷ ዊልያም ሩቶ ላይ ተመስርቶ የነበረዉን ክስ ማቋረጡን አስታዉቋል።

ከእሳቸዉ ጋርም በጎርጎሪዮሳዊዉ 2007/2008 ከተካሄደዉ ምርጫ በኋላ በተፈጠረዉ ዉዝግብ እና በደረሰዉ የሰዉ ሕይወት እና የንብረት ጉዳት ጀርባ እጃቸዉ አለበት ተብሎ በተመሳሳይ ኬንያዊ ጋዜጠኛ ጆሹዋ ሳንግም ክስም ዘግቷል። የፍርድ ቤቱ ዳኞች በድምጽ ብልጫ የቀረበዉ ማስረጃ በቂ እንዳልሆነ ቢወስኑም አቃቤ ሕግ ተጨማሪና በቂ ማስረጃ ካቀረበ እንደገና ሊታይ እንደሚችልም ጠቁመዋል። የፍርድ ቤቱ አቃቢተ ሕግ ፋሱ ቤንሱዳ በትዊተር መልዕክት ይፋ እንዳደረጉት ምስክሮቹ ወከባ ደርሶባቸዋል። በሌላ በኩል የኬንያ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉልበት ሰጪ ንጥረ ነገር ተጠቅመዋል የተባሉትን አትሌቶች በሚመለከት ምላሽ እንዲያቀርብ የተሰጠዉ አብቅቶአል። በእነዚህ ነጥቦች ላይ ናይሮቢ ከሚገኘዉ ጋዜጠኛ ፋሲል ግርማ ጋር በአጭሩ በስልክ ተወያይተናል።

ሲል ግርማ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic