የኬንያ ቀዉስና ዲፕሎማሲያዊዉ ጥረት | አፍሪቃ | DW | 10.01.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኬንያ ቀዉስና ዲፕሎማሲያዊዉ ጥረት

ናይሮቢ የዉጥረት፤ ግጭት፤ የሹመት-ሽረት፣ ፍትጊያ፣ የተሰላፊ-አድማ ያድማ በታኝ ፍጥጪያ፣ የዲፕሎማሲ-ሽምግልና ስብሰባ ዉይይት ማዕከልነቷ እንደደመቀ---

ከዚሕም በሕዋላ ዉዝግቡ ቀጥሏል

ከዚሕም በሕዋላ ዉዝግቡ ቀጥሏል

የኬንያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች በምርጫ ዉጤት ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።አወዛጋቢዉ ምርጫ እንዲደገም የሚቀርብልቸዉን ጥያቄ እንቢሽ ያሉት ፕሬዝዳት ምዋዪ ኪባኪ የሰየሙትን ካቢኔ ዛሬ ቃለ መሐላ ፈፅሟል።የተቃዋሚዉ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲጋ ደጋፊዎች ባንፃሩ ዛሬ ኪባኪን በቃወም ናይሮቢ ዉስጥ ታላቅ ሠልፍ አድርገዋል።ተቀናቃኝ ሐይላትን ለመሸምገል የተጀመረዉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረትም አልተቋረጠም።ነጋሽ መሐመድ ሥለ ኬንያ የዛሬ ማርፈጃ የሚከተለዉን ዘገባ አጠናቅሯል።


ናይሮቢ የዉጥረት፤ ግጭት፤ የሹመት-ሽረት፣ ፍትጊያ፣ የተሰላፊ-አድማ ያድማ በታኝ ፍጥጪያ፣ የዲፕሎማሲ-ሽምግልና ስብሰባ ዉይይት ማዕከልነቷ እንደደመቀ ሁለተኛ ሳምንቷን አገባደደች።ከዩናይትድ ስቴትስዋ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጄንዳይ ፍሬዘር፣-ናቸዉ።

የወቅቱ የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበርና የጋና ፕሬዝዳት ጆን ኩፉር-ናይሮቢ ናቸዉ። የደቡባዊ አፍሪቃ የልማት ማሕበረሰብ ሊቀመንበርና የዛምቢያዉ ፕሬዝዳት ሌቪ ምዋናዋሳ-ናይሮቢ ናቸዉ። የቀድሞዉ የታንዛኒያ ፕሬዝዳት ቤንጃሚን ኢንካፓ፣ የቀድሞዉ የሞዛምቢክ ፕሬዝዳት ዮአኪም ቺሳኖ እና ሌሎችም ናይሮቢ ናቸዉ።- የዶቼ ቬለ የኪሲዋሕሊ ቋንቋ አገልግሎት የናይሮቢ ዘጋቢ አልፍሬድ ኪቲ እንደሚለዉ ሁሉም የኬንያ ፖለቲከኖችን ታረቁ ይላሉ።

«ችግሩን ለማስወገድ እና በሐገሪቱ ሠላም ለማስፈን ፕሬዝዳት ምዋዪ ኪባኪ እና ራይላ ኦዲንጋን ለመሸምገል የሚደረገዉ ዲፕሎማሲ ጥረት እንደጠናከረ ነዉ።»

በርግጥም ተጠናክሯል።ትናት ከፕሬዝዳት ኪባኪ ጋር ሲመክሩ፣ ሲነጋገሩ የዋሉት የዉጪ ሹማምንት ዛሬ ከተቃዋሚ ራይላ ኦዲንጋ ጋር ተነጋግረዋል።ንግግር-ዉይይቱ ለፍሬ ይበቃል-የሚለዉ ተስፋም በአልፍሬድ አገላለፅ ከፍተኛ ነዉ።

«ጉጉቱ እዚሕ ከፍተኛ ነዉ።በሁለቱ ወገኖች በአቶ ኦዲንጋና በፕሬዝዳት ኪባኪ መካካል መቀራረብ ይኖራል የሚለዉ ተስፋ ትልቅ ነዉ።ሕዝቡም የሚጠብቀዉ ይንኑ ነዉ።ሁለቱ መሪዎች ችግሩን ማስወገድ አለባቸዉ ነዉ-የሚለዉ።ፕሬዝዳንታዊዉ ምርጫ በድጋሚ ቢደረግ ጥሩ ነዉ-የሚለዉ የሕዝብ አስተያየት አሁን ጠንክር ያለ ነዉ።ለዚሕ ደግሞ ሁለቱ መሪዎች መስማማት አለባቸዉ ባይ ነዉ።»

ጉጉት ተስፋዉ ያይል-እንጂ ከሸምጋዮቹ አንዱ የቀድሞዉ የሞዛምቢክ ፕሬዝዳት ዮአኪም ቺሳኖ እንደመሰከሩት እስከ ዛሬ ከጉጉት-ተስፋ ያለፈ ነገር የለም።

«የኬንያን ሕዝብ እና መሪዎች ለማግባባት እኔ ከሌሎች ሰወስት የአፍሪቃ የቀድሞ ፕሬዝዳቶች ጋር ሆኜ እየጣር ነዉ።እዚሕ ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ከተቀናቃኝ ሐይላቱ ጋር ተገናኝተናል።ይሁንና እስካሁን ተጨባጭ ዉጤት ላይ አልደረሰንም።መጠበቅ አለብን።ዉይይቱ እንደቀጠለ ነዉ።ከእንግዲሕ ምናልባት ላንድ ሁለት ቀን መቀጠል ይኖርብን ይሆናል።ከዚያ ብሕዋላ ነዉ-መናገር የምንችለዉ።ለጊዜዉ ግን ምንም የተወሰነ ነገር የለም።»

ፕሬዝዳት ኪባኪ ግን የወሰኑ ይመስላሉ።ድጋሚ ምርጫ ወይም የድምፅ ቆጠራ የሚለዉን ሐሳብ እንቢኝ እንዳሉ።እንዲያዉም መላዉን ኬንያ የሚያገለግል ያሉት ካቢኔ አባላት ዛሬ ቃለ መሐላ አፅፈፅመዋል።የጎደሉ ሚንስትሮችን ባጭር ጊዜ ለሟሟላትም ወስነዋል።ኦዲንጋም፣ ከኪባኪ ጋር ብሔራዊ ያንድነት መንግሥት መመስረቱን እንቢኝ ብለዋል።ደጋፊያቸዉ አሰልፈዉ ምርጫዉ እንዲደገም የሚጠይቅ ደጋፊያቸዉ ዛሬ