የኬንያ ምርጫ | አፍሪቃ | DW | 29.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የኬንያ ምርጫ

ወጣት ኬንያውያን በእጩዎቻቸው እንደተሰላቹ ይሰማል። ምርጫም በኬን ደም አፋሶ በኪኩዩ እና ሉዎ ጎሳዎች መካከል ፖለቲካዊ ውጥረት ፈጥሮ ያውቃል። ዘንድሮስ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:10

የኬንያ ምርጫ

ከብዙ አመታት በፊት በኬንያ እንዲህ ሆነ፦አገሪቱን ቅኝ ይገዙ የነበሩት እንግሊዞች ጃራሞጊ ኦጊንጋ ኦዲንጋ ሥልጣን እንዲይዙ ግብዣ አቀረቡላቸው። እርሳቸው ግን አሻፈረኝ አሉ። ጃራሞጊ ኦጊንጋ ኦዲንጋ "ኬንያ መሪዋ ጆሞ ኬንያታ ታስረውባት ነፃ ልትሆን አትችልም" ሲሉ መለሱላቸው። ኬንያም ነፃ ወጣች እና አንዳቸው ፕሬዝዳንት ሌላኛው ምክትል ለመሆን በቁ። ወዳጅነታቸው ግን አልዘለቀም። በጎርጎሮሳዊው 1966 ጆሞ ኬንያታ እና ጃራሞጊ ኦጊንጋ ኦዲንጋ ተቃቃሩና ዛሬ በኬንያ የሰፈነው የኪኩዩ እና ሉዎ ጎሳዎች ፖለቲካዊ ውጥረት ተወለደ። ከአመታት በኋላ እነሆ ዘንድሮ ሁለቱ ተቀናቃኝ ቤተሰቦች በመጪው የኬንያ ምርጫ ለሥልጣን ይፎካከራሉ። የራይላ አባት ጃራሞጊ ኦጊንጋ ኦዲንጋ የመጀመሪያው የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ነበሩ። ላለፉት አራት አመታት አገሪቱን ያስተዳደሩት ኡሑሩ በአንፃሩ የጆሞ ኬንያታ ልጅ ናቸው። ኬንያ ከብሪታኒያ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ስትወጣ የመሯት የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት።

 ገበያው ንጉሴ 

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች