የኬንያ ምርጫ ዉጤትና ዉዝግብ  | አፍሪቃ | DW | 16.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኬንያ ምርጫ ዉጤትና ዉዝግብ 

NASA በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉን የተቃዋሚዎች ሕብረት ወክለዉ ለፕሬዝደንትነት ተወዳድረዉ የነበሩት ኦዲንጋ ባላጋራቸዉ ፕሬዝደንት ኡሑሩ ኬንያታ ያሸነፉት የኮምፒዉተር ሰነድን አዛብተዉ ነዉ ባይ ናቸዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:00
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:00 ደቂቃ

ኦዲንጋ የፍርድ ቤት ሙግት ሊገጥሙ ነዉ

የኬንያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሕብረት መሪ ራይላ ኦዲንጋ ባለፈዉ ሳምንት የተደረገዉን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዉጤት ለማሻር በፍርድ ቤት እንደሚሟገቱ አስታወቁ። NASA በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉን የተቃዋሚዎች ሕብረት ወክለዉ ለፕሬዝደንትነት ተወዳድረዉ የነበሩት ኦዲንጋ ባላጋራቸዉ ፕሬዝደንት ኡሑሩ ኬንያታ ያሸነፉት የኮምፒዉተር ሰነድን አዛብተዉ ነዉ ባይ ናቸዉ። ፕሬዝደንት ኬንያታ ምርጫዉን በ54 ከመቶ ድምፅ ማሸነፋቸዉን የሐገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታዉቋል። በተያየዘ ዜና የኬንያ መንግስት፤ መንግሥታዊ ያልሆኑ ሐገር በቀል ድርጅቶች እንዲዘጉ ያሳለፈዉን ዉሳኔ ለሰወስት ወራት ያክል አነሳ። ስለ ኬንያ የምርጫ ዉዝግብ የፖለቲካ ተንታኝ ፍቅረማርያምን በሥልክ አነጋግሬያቸዉ ነበር።

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች