የኬንያ ምርጫና ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ | አፍሪቃ | DW | 31.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኬንያ ምርጫና ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ

ለሁሉም ክፍት የሆኑትን ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ በኬንያ የጎሳ ፖለቲካ ለማራመድ አለአግባብ የሚጠቀሙባቸውም አሉ ። ከአሁኑ እንኳን ባለፈው ምርጫ ወቅት የነበረውን አይነት ስሜት የሚቀሰቅሱ ፅሁፎች ይወጣሉ ። ባለፈው ምርጫ ከተከሰተው ብጥብጥ በኋላ ጥላቻን የሚቀሰቅሱ ንግግሮች በህግ ተከልክለዋል ።

በኬንያ የፊታችን መጋቢት ምርጫ ይካሄዳል ። ምርጫው የሃገሪቱን ዲሞክራሲ የሚያጎለብት ትልቅ እርምጃ ተደርጎ ነው የተወሰደው ። በመጋቢቱ ምርጫም በርካታ የአዲሱ ህገ መንግሥት ማሻሻያዎች ተግባራዊ ይሆናሉ ። የምርጫ ጣቢያዎች ቅነሳ ፣ ለሴቶች የተሰጠው ኮታ ፣ እና የቀበሌ ምክር ቤቶች መቋቋም እስካሁን ለትልቁ የፕሬዝዳንትነት ሥልጣን የሚደረገውን የኃይል እርምጃን ያካተተ ትግል ለመከላከል እገዛ ያደርጋሉ ተብሎም ይታመናል ። በሌላ በኩል ባለፉት 5 አመታት በርካታ ኬንያውያን ኢንተርኔትን በምርጫ ዘመቻ በንቃት ለመሳተፍ እየተጠቀሙበት ነው ። የዶቼቬለዋ ማያ ብራውን ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ በኬንያ ዲሞክራሲ እድገት ላይ ስላሳደሩት ተፅዕኖ ያዘጋጀችውን ዘገባ ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ማዕከላዊ ናይሮቢ በሚገኝ ጎዳና በየምሽቱ ከሥራ ተባዕት ኬንያውያን ፣ ማን ለምን የትኛውን እጩ ተወዳዳሬ እንደሚደግፍ ይነጋገራሉ ።

A woman surfs the web at an internet center on March 13, 2012 in Tunis on the first National Day for Internet Freedom in Tunisia. Tunisian President Moncef Marzouki denounced on March 13 'enemies of democracy' and those who refused the results of the October 23, 2011 elections in Tunisia during his address to mark the first day of cyberliberty. AFP PHOTO / FETHI BELAID (Photo credit should read FETHI BELAID/AFP/Getty Images)

የፌስቡክ ተጠቃሚ

በየጎዳናው የሚሆነው በተመሳሳይ ጊዜ በኢንተርኔት የሚካሄደውን ህይወት ያለው ውይይት ያንፀባርቃል። ኬንያውያን ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ ማለትም ብሎጎች ፌስቡክ ና ትዊተርን በፖሊሲዎች ላይ ክርክር ለማካሄድ ይጠቀሙባቸዋል ። ፖለቲከኞችም ከረዥም ጊዜ አንስቶ የዚሁ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ናቸው ። የት እንዳሉና ምን እንደተናገሩ በየሰአቱ በፌስቡክ ያሳውቃሉ ። አንዳንዶች ደግሞ በትዊተር አጫጭር መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ ከህዝቡ ጋርም ይነጋገራሉ ። በዚህ ሂደትም ብዙዎች ትችቶችን ይቀበላሉ ። ኬንያዊው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ና የመብት ተሟጋች ምዋሊሙ ማቲ ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ ጠቃሚ ጎኖች እንዳሏቸው ሁሉ ጎጂ ጎኖች እንደማያጡም ይናገራሉ ።

« በርካታ ፖለቲከኞች ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛን በምርጫ ዘመቻ መድረክነት እየተጠቀሙበት ነው ። ስለራሳቸው ና ስለእቅዳቸውም ይበልጥ እየተናገሩበት ነው ። ሆኖም በማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ ስለ ፖለቲከኞች እቅድ መናገር የሚቻለው የተገደበ ነው ። ያም ሆኖ እንደሚመሰለኝ ይህ ለፖለቲከኞቹ አነሰም በዛም ሜዳውን ያስተካክላል ። ምክንያቱም ሃብት የሌላቸው እጩ ተወዳዳሪዎቹም ከህዝቡ ጋራ የሚገናኙበትን መንገድ እንዲፈልጉም ያስችላቸዋል »

ሆኖም ማቲ እንደሚሉት ተፅእኖው ኤሌክትሪክና የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት በሚችሉ ከተሞች ብቻ የተገደበ ነው ። ከዛሬ 5 አመቱ የኬንያ ምርጫ ወዲህ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር በጣም አድጓል ። በኬንያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር መረጃ መሰረት 14 ሚሊዮን ኬንያውያን ማለትም ከህዝቡ 30 በመቶው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው ። ከ 5 አመት በፊት ግን ወደ 5 በመቶ ገደማ ብቻ ነበር ።

Boniface Mwangi, politischer Aktivist aus Kenia. Copyright und zugeliefert von: DW/Maja Braun, 28. November 2012 in Nairobi, Kenia

ቦኒፌስ ምዋንጊ

በኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ማደግ በርካታ የሲቪል ማህበራት ብዙ ጥቅሞች አግኝተዋል ። ይህም በአንዳንዶች አስተያየት የፖለቲካውን ምህዳር አስፍቶታል ። ቦኒፌስ ምዋንጊን የመሳሰሉ አንዳንድ የመብት ተሟጋቾች ፌስቡክን ለሠላማዊ ሰልፍ ጥሬ ይጠቀሙበታል ። ሆኖም በርሳቸው አስተያየት ፌስቡክ ከዚህ ለላቀ ጉዳይ በቂ አይደለም ።

« ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ የሚያሳድሩት ተፅእኖ በጣም ዝቅተኛ ነው ። ለመጮህና ድምፅን ለማሰማት ጥሩ ቦታ ነው ። ሆኖም ውጤታማ መሆኑን በጣም እጠራጠራለሁ ። ሌላው ለአሁኑ አሳሳቢው ጉዳይ ትክክለኛው ኃይል የሚገኘው ከነዚህ መድረኮች ውጭ መሆኑ ነው ። በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በትዊተር ከሚፃፉ ስሞታዎች ይልቅ ሰዉን አሰባስቦ መፈክር ይዞ ወደ ጎዳና መውጣቱ የተሻለ ነው »

በኬንያ ማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን እንደሚነበበውና እንደሚሰማው ፕሬዝዳንታዊ እጩ ማርታ ካሩዋ የተሻለ የማሸነፍ እድል ሊኖራቸው ይገባ ነበር ። የቀድሞዋ የፍትህ ሚኒስትር ካሩዋ እነዚህን መድረኮች በመጠቀም ቀዳሚዋ ከመሆናቸውም በላይ ለምርጫ ዘመቻቸውም ብዙ ገንዘብ አሰባስበውበታል ። ሆኖም ከህዝብ በተሰበሰበ አስተያየት መሰረት ግን አሁንም ወደ ኃላኛው ስፍራ ላይ ነው የሚገኙት ። ለሁሉም ክፍት የሆኑትን ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ በኬንያው የጎሳ ፖለቲካ ለማራመድ አለአግባብ

የሚጠቀሙባቸውም አሉ ። ከአሁኑ እንኳን ባለፈው ምርጫ ወቅት የነበረውን አይነት ስሜት የሚቀሰቅሱ ፅሁፎች ይወጣሉ ። ባለፈው ምርጫ ከተከሰተው ብጥብጥ በኋላ ጥላቻን የሚቀሰቅሱ ንግግሮች በህግ ተከልክለዋል ። በርካታ ተቋማት እነዚህ መሰል ንግግሮች ወይም ፅሁፎች ህጉን የሚፃረሩ መሆን አለመሆናቸውን ይከታተላሉ ። ከነዚህም አንዱ ብሔራዊ የህብረትና የውህደት ኮሚሽን ነው ። ሊቀ መንበሩ ማዛሌንዶ ኪቡንጃ በማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ የሚሰራጩ መልዕክቶች ጥንቃቄዎች የሚያሻቸው መሆናቸውን ነው የሚያሳስቡት ።

« በምንም አይነት ጉዳይ ላይ ዘመቻ ስናካሂድ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ። የምርጫ ዘመቻ በሚካሄድበት መንገድ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል ። ያ ብቻ አይደለም ግለሰቦች የሚናገሩትም ሁሉ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል ። የፖለቲከኞቹ ንግግር የተገደበ ሊሆን ይገባል ።ምክንያቱም ምን ሊያጋጥም እንደሚችል አታውቅም »

መንግሥት ማህበራዊ ብዙሃን መገናኛ እንደሚከታተል በቅርቡ በሰጠው ዝርዝር መግለጫ አስታውቋል ። ዘለፋም ሆነ ማስፈራሪያ ያላቸው መልዕክቶች ፀሃፊዎች ከባድ ቅጣት ይተላለፍባቸዋል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic