የካንኩን የአየር ንብረት ጉባኤ | ጤና እና አካባቢ | DW | 30.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የካንኩን የአየር ንብረት ጉባኤ

ዓለም ዓቀፉ የተመድ የአየር ንብረት ለዉጥ ላይ የሚነጋገረዉ ጉባኤ አይደርሱ ቀጠሮዉ ደርሶ ትናንት ሜክሲኮ ካንኩን ከተማ ላይ ተጀምሯል።

default

የግሪንፒስን መልዕክት የተሸከመችዉ ፊኛ በካንኩን ሰማይ ላይ

በዚህ ጉባኤ ላይ ወደሁለት መቶ ከሚሆኑ አገራት የተዉጣጡ ሃያ አምስት ሺ ገደማ ተሳታፊዎች ናቸዉ የሚገኙት። ምንም እንኳን አምና በተስፋ ተጠብቆ እንደታሰበዉ ያልተጠናቀቀዉ ዴንማርክ ኮፐንሃገን ላይ የተካሄደዉ ጉባኤ ጥሩ ያልሆነ ስሜትን ቢጭንበትም ዘንድሮ ቢያንስ ለሚቀጥለዉ ዓመት ጉባኤ መንደርደሪያ የሚሆን ተገቢ መስመር ያስይዛል ተብሎ ይገመታል። የሚቀጥለዉ ዓመት የዚህ ጉባኤ አስተናጋጅ አፍሪቃዊቷ አገር ደቡብ አፍሪቃ ትሆናለች።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ