የካንኩኑ ጉባዔና አሳሳቢው የዓለም የአየር ንብረት ጉዳይ፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 08.12.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የካንኩኑ ጉባዔና አሳሳቢው የዓለም የአየር ንብረት ጉዳይ፣

በደንማርክ መዲና በኮፐንሄገን፣ ከኅዳር 28 እስከ ታኅሳስ 9 ቀን 2002 ዓ ም፣ በዓለም ውስጥ በዓይነቱ የመጀመሪያ የተባለው ዐቢይ የዓለም የአየር ንብረት ጥበቃ ነክ የመሪዎች ጉባዔ ከተካሄደ ወዲህ ፣ በቀጣይነት ካንኩን ሜክሲኮ ላይ ፣ 194 መንግሥታት የተወከሉበት ተመሳሳይ ጉባዔ ከተጀመረ እንሆ ዛሬ 10ኛ ቀኑን ይዟል።

default

የአታካማ ምድረ-በዳ፣

ስለ ዓለም የአየር ጠባይ መዛባትና ስለሚያስከትለው ሳንክ፣ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በሰፊው ሆኗል የሚነገረውም ፤ የሚመከረውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አጠቃላይ ጉባዔም፣ ሊሠናበት 23 ቀናት የቀሩት ጎርጎሪዮሳዊው 2010 ዓ ም ፣ የብዝኀ-ህይወት መታሰቢያ ዘመን ተብሎ እንዲዘከር ማድረጉ የሚዘነጋ አይደለም። ከዚያ ቀደም ሲል ከ 2007 -2009 ዓለም አቀፍ የፕላኔት ምድር መታሰቢያ ዘመን ሲባል፤ 2008 የንፅህና አጠባበቅ ትኩረት የሚደረግበት ዘመን፣ 2009 በተጨማሪ የሥነ ፈለክ መታሰቢያ ዘመን ተብሎ እንደነበረ የምናስታውሰው ነው። የፕላኔት ምድር እንዲሁም የብዝኀ-ህይወት መታሰቢያ የተያያዘ ነው። የብዝኀ-ህይወት ኅልውና በአየር ንብረት ላይ የተመረኮዘ መሆኑ የሚታበል አይደለም። አየር ሲባል ደግሞ በየብስ ፣ በውቅያኖስና በጠፈር ያለውን የሚመለከት ነው።

በየብስ የአየር ንብረትን በተመለከተ ሊተኮርበት የሚገባ አንደኛው እጅግ አሳሳቢ ችግር የበረሃ መስፋፋት ነው። የተባበሩት መንግሥታት የበረሃ መስፋፋት እንዲገታ የተስማማበት ን ጉዳይ አስፈጻሚው ባለሥልጣን እንደሚሉት፤ ምድረበዳዎችን በአመዛኙ በረሃ ከመሆናቸው በፊት ወደነበሩበት መመለስ የሚቻል አይደለም፤ ይሁንና ፣ በረሃ የመሆን አደጋ የተጋረጠባቸውን ቦታዎች፣ ከጥፋት ለማዳን በጎ የፖለቲካ ፈቃድ፣ ትብብርና ኅብረት ካለ አያዳግትም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ እ ጎ አ ከ 2010 እስከ 2020 በሚመጡት 10 ዓመታት የበረሃ መስፋፋትን ለመግታት ተጋድሎ የሚደረግበት ዘመን እንዲሆን ማወጁ ቢታወስም፤ በያመቱ፤ 12 ሚሊዮን ሄክታር (30 ኤከር)ማለት የግሪክን ወይም በአፍሪቃ የቤኒንን ያክል ስፋት ያለው ለግብርና ተስማሚ የሆነ መሬት፣ ከጥቅም ውጭ የመሆን ዕጣ እየገጠመው ነው። በምድራችን ወይም በምንኖርባት ፕላኔት ፣ 40 ከመቶ በላይ የሚሆነው የብስ ደረቅ ነው። ከዓለም ህዝብ መካከል ከየ 3ቱ አንዱ የሚኖረው (በአጠቃላይ 2,1 ቢሊዮን ህዝብ መሆኑ ነው) በተጠቀሰው ደረቅ የዓለም ክፍል ነው። 90% ይኸው ቦታ የሚገኘው ደግሞ እጅግ የከፋ ድህነት በተጠናወታቸው በአዳጊ አገሮች ሲሆን አንድ ቢሊዮን ያህሉ ኑዋሪዎች በበረሃ መስፋፋት ሳቢያ ፣ እህል ማምረት የሚችሉበት ሁኔታ አደጋ እንደተቃጣበት ነው። ምድራችን እየጋለች መሄድዋ ከቀጠለ ፣ የምድረበዳዎች መስፋፋት ይቀጥላል። የምግብና የሚጠጣ ውሃ እጦትም እየተባባሰ ይሄዳል። ጠበብት እንደሚሉት እ ጎ አ በ 2050 የዓለም ህዝብ ብዛት 9 ቢሊዮን ስለሚደርስ፤ ለግብርና የሚሆነውን መሬት ሁሉ ከጥፋት ማዳን ተገቢ ይሆናል። ከኮፐንሄገን የቀጠለው የካንኩን ጉባዔ፣ ለምድር ግለት ሰበብ የሆነው የተቃጠለ አየር (CO2) ይገታ ዘንድ፣ ስምምነት ላይ ይደርስ ይሆን?

(ድምፅ)

በጉባዔው በመሳተፍ ላይ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን ተሳታፊዎች መካከል፤

የ ኤኮ የሸማቾች ማኅበር ዋና ሥራ መሪ ፣ ሻምበል ገ/መድኅን ቢረጋ---

በሰፊው የክፍላተ ዓለም የብስ የድርቅ መስፋፋት ሲያሠጋ ፣ በዓለም ዙሪያ በዛ ያሉ ደሴቶች መጠኑ ከፍ እያለ በሚሄደው የውቅያኖስ ውሃ ሳቢያ እንዳይሰጥሙ ይሠጋሉ። ባህር የሚያዋስኑ የጠረፍ ከተሞችም እንዲሁ!

(ድምፅ)

በዓለም ዙሪያ የውቅያኖሶች የብክለት ደረጃ፣

(ድምፅ)