የካናዳ መንግሥት ወደኢትዮጵያ ለሚያጓዙ የሰጠዉ ማስጠንቀቂያ | አፍሪቃ | DW | 25.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የካናዳ መንግሥት ወደኢትዮጵያ ለሚያጓዙ የሰጠዉ ማስጠንቀቂያ

የካናዳ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ። በካናዳ መንግሥት ድረ ገጽ ላይ የወጣዉ ማሳሰቢያ ኢትዮጵያን ባጠቃላይ የሚመለከት ማሳሰቢያ እንደሌለዉ በመጠቆም፤ ባለለዉ አስጊ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ዜጎቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:13
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:13 ደቂቃ

ዜጎቹ እንዲጠነቀቁ አሳስቧል፤

 በዚሁ መሠረትም ወደ ኤርትራ፤ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ሶማሊያ አዋሳኝ የድንበር አካባቢ ፈፅሞ እንዳይሄዱ ሲያስጠነቅቅ፤ ወደ ኬንያ የድንበር አካባቢ እና ኗሪዎች ከፀጥታ ኃይላት ጋር ያላቋረጠ ግጭት ዉስጥ ናቸዉ ወዳለዉ ወደ ሰሜን ጎንደር ደግሞ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ ዜጎቹ እንዳይሄዱ አሳስቧል። ዜጎቹ እንዳይሄዱ ያሳሰበበትን አካባቢ በተናጠል በመዉሰድም አሉ ስላላቸዉ የፀጥታ ስጋቶችም ዘርዝሯል። ይህን ማሳሰቢያ አልፈዉ የሚሄዱ የካናዳ ዜጎችም ኃላፊነቱ የራሳቸዉ እንደሚሆን አጥብቆ አሳስቧል። ከቶሮንቶ ዘጋቢያችን አክመል ነጋሽን ስለጉዳዩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

አክመል ነጋሽ /ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic