የካስትሮ አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ  | ኢትዮጵያ | DW | 28.11.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የካስትሮ አስተዋጽኦ በኢትዮጵያ 

ባለፈዉ ቅዳሜ በ90 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ፊደል ካስትሮ  ለበርካታ የአፍሪቃ ሀገሮች የነፃነት ትግል ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳደረጉ ይነገራል። ከ1969-1970 በተካሄደው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጦርነት ወቅት የካስትሮ አስተዳደር ኢትዮጵያን በማገዝ ብዙ ወታደሮችንና የጤና ባለሙያዎችን ወደ ኢትዮጵያ ልኮ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:44
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:44 ደቂቃ

ፊደል ካስትሮ

በዚህ ጦርነት የተሳተፉ የኢትዮጵያውያን ወታደሮች ልጆች ከጦርነቱ በኋላ የትምህርት ዕድል አግኝተዉ በኩባ ተምረዋል።የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዩሱፍ ኑሪዬ «አርበኛና ጀግና መሪ» በሚሏቸው በካስትሮ ሞት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸዉ ይናገራሉ። በኢትዮጵያና ሶማሊያ ጦርነት ጊዜ ኩባ ኢትዮጵያን በመሣርያና በወታደሮች እንድታግዝ፣ «አገሪቷ ነፃነቷን እንድታስከብር አድረገዋል» ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ይናገራሉ። በርሳቸው አስተያየት አሁን ግን ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር የቀድሞው ዓይነት ግንኑነት አላት ብለው አሳያስቡም።

«ፊዴል ካስትሮ ለኢትዮጵያ ትልቅ ባለዉለታ ናቸዉ» ያሉን ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሌላ የአዲስ አበባ ነዋሪ  ፣ በፊት በደርግ ስርዓት ላይ በነበረው ጥላቻ መንስኤ የካስትሮ ዉለታ አሁን በኢትዮጵያ ዉስጥ «ብዙም ሽፋን አለገኘም» ይላሉ። በኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ዉስጥ የአየር መቃወምያ ላይ ስሰራ ነበርኩ የሚሉት እኝህ አስተያየት ሰጭ ደግሞ በመከላከያው ዘርፍ የኩባ አስተዋፅፆ ቀላል የሚባል እንዳልነበረ ነው የሚናገሩት።

በአድስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ዮናስ አሽኔ የካስትሮን «ሞት ሳይሆን ህይወቱን ነዉ የምናስበዉ ይላሉ። በኢትዮ/ኩባ ግንኙነት ላይ ጥናት በመካሄድ ላይ ያሉት  አቶ ዮናስ «ኩባ እንደ አብዮታዊ ወይም የነፃነት ደሴት ተምሳሌት» እንደምትታይ ተናግረው በኢትዮጵያ አብዮት ዉስጥ ተምሳሌትነቱ ትልቅ ነበር ብለዋል።

በፌስቡኩ ደረ ገፃችን ላይ ስለ ፊደል ካስትሮ ሞትና ለኢትዮጵያ ስላደረጉት አስተዋፅፆ አስተያየታቸዉን ካጋሩን ውስጥ «በእውነቱ ትልቅ ባለውለታችን ነበሩ አቶ ካስትሮ አፈሩን ያቅልልላቸው» ያሉ ይገኙበታል «የቀድሞውን የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን እግዚአብሔር ያፅናዎት በሉልን » ሲሉ አስተያየታቸዉን አያጋሩንም አሉ።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ  
 

Audios and videos on the topic