የካርኒቫል ፈንጠዝያ | ዓለም | DW | 20.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የካርኒቫል ፈንጠዝያ

ግሪኩ፥ላቲኑ፥ ኢጣሊያዉ እንደሚለዉ ካርኒቫል-የሥጋ መሰነባቸነዉ።ከሮብ ጀምሮ ፆም ነዉና።

default

ኮሎን-ሰወስቱ ተመራጮች

ባብዛኛዉ በካቶሊክ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረዉ የካርኒቫል የአደባባይ ፌስታ ትናንት ጀርመን ዉስጥ ተጀምሯል።በአሉ በተለይ የራይን ወንዝ አቋርጦ በሚያልፍባቸዉ በኮሎን፥ ዱሰልዶርፍና ቦንን በመሳሳሉ ከተሞች በድምቀት እየተከበረ ነዉ።በአለተኞች አርባ-ቀናት የሚቆየዉ የካቶሊክ ክርስትና ፆም ከመጀመሩ በፊት ባደባባይ እየተበላ፥ እየተጠጣ የሚዘፈን የሚጨፈርበትን ፌስታ እንደወትሮዉ ለማክበር ብዙ መጣር መሞከራቸዉ አልቀረም።ይሁንና አለምን የመታዉ የምጣኔ ሐብት ድቀት የዘንድሮዉን በአል ተጫጭኖታል።ነጋሽ መሐመድ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

እንደ ጥንተ-አመጣጥ መቼነቱ፥ እንደ ስያሜዉ-እንዴትነት ብዙነት ሁሉ አጀማመሩም ወጥ ብያኔ አላገኘም።አንዳዶች አስራ-አንደኛዉ ወር፥ በአስራ-አንደኛዉ ቀን፥ አስራ-አንድ ሰአት ላይ ይጀመራል ይሉታል።በነሱ አቆጣጠር ሕዳር-አስራ አንድ-አስራ-አንደ ሰአት።በዚሕ የማይማሙ አሉ።ሁሉም ግን አስራ-አንድን ይወዱታል።ወይም ከዚያ ይጀምራሉ።በአሉ-ኮሎን ላይ ላደባባይ ፌስታ-ሲያሳድም ትናንም ሲያሳድም አስራ አንድ ሰአት (በኛ ከቀኑ አምስት)።ከአስራ-አንድ ቁጥር ተጀመረ።

ድምፅ

"11, 10,9,8,7,6,5,4,3,2,1,"

በአለተኞች-ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንደ ሆነ እንደሚሆነዉ -ሳይሆን እንደሚመኘዉ ይለብሳል።-ያጌጣል። ሰይጣን በየትኛዉም እምነት እርኩስ ነዉ-ራሱ ሰይጣን፥ ጭራቅ፥ ቡዳ፥ ጥንቸል፥ አይጥ፥ ድመት፥ ተኩላ ድብ ብዙ ነዉ-እንደሚደሰትበት ይልበስላል።ይኳኳላልም።

የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎችን ለማጥፋት ከበርቴዉ አለም ያዘመተዉ ጦር-አደን ባሕረ-ሰላጤ ላይ እየተፋለመ ነዉ።በአፈ-ታሪክ የሚነገረዉን የባሕር ላይ ዘራፊን የሚመኝ-እንደ ዘራፊዉ የሚለብስ ብዙ ነዉ።እንደ ቄስ፥ እንደ ሼኽ፥ እንደ ሐኪም፥ እንደ ጄኔራል -ምኑ ቅጡ።አዉሮጶች ከፈረንሳይ አብዮት፥ አብዛኛዉ አለም ከሩሲያ አብዮት ወዲሕ የንጉስ-መሳፍንት አጋዛዝን እንቢኝ ብለዉ ሪፐብሊክ መስርተዋል።

ልዑል-ልዕልት መሆን የሚመኙት ከስም በላይ እንደማያዉቋቸዉ ለብሰዉ፥ ዘዉድ ደፍተዉ ካባ ጭነዉ አደባባይ ይወጣሉ።የአመቱን በአል-የሚባርከዉም በአለተኛዉ የአመቱ ልዑል አድርጎ የሚመርጠዉ ነዉ።ለኮሎን-ዘንድሮ የተመረጡት ልዑል ሐንስ- ጊዮርግ ቀዳማዊ እንደሳቸዉ ሁሉ የአመቱ ገበሬ፥ የአመቷ ኮበሌ ሆነዉ-የተመረጡት ግራ ቀኝ አስቀመጥጠዉ እንግዶቻቸዉን ተቀበሉ።

ድምፅ

«የከልኖቹ ሰዎስት እንግዶች ከልብ በመነጨ መንፈስ እንኳን በደሕና መጣችሁ ይላሉ።የአዉራ-ጎዳናዉ ካርኒቫል ሲጀመር በመገኘታችሁ ታላቅ ክብርና ደስታ ይሰማናል።ታላቅ ክብረ-በአል መሆኑን አስታዉቁ።ሁላችንም ባንድነት እናክብር።በመላዉ አለም ወደር የማይገኝለት ፌስታ ነዉ።»

ልዑሉን መቃወም አይቻል-ካልሆነ በስተቀር እንጂ የኮሎኑ ድግስ-የሪዮ ዲ የኔሮዉን ያክል እንኳን አይደምቅም።ብቻ-ሙዚቃ ጭፈራ-ዳንሱ ቀለጠ።

ድምፅ

የተራቆተ፥ በቀለማት፥ የተዥጎረጎረ፥ በፀሐይ-የጋለ አካልን በአልኮል የሰገረ-አዕምሮ የሳምባ ዳንስ ሰደቻ የሚያሰብቀዉ የብራዚሎቹ ፌስታ እሁድ እስኪግም ግን ጀርመን ከለኖች-አንደኞች ናቸዉ።እንደ ብራዚሎች ለፀሐይ አልታደሉም።እሷማ ተናዳለች።

ድምፅ

«እይ-ፈጣሪዬ ለምንድን ነዉ-ዛሬ የሚዘንበዉ? በጣም ያምራል።ዝናብ ባይጥል ኖሮ ደግሞ የበለጠ ቆንጆ ይሆን ነበር።ለምን? እንዲያ ቢሆን ይበልጥ ያበረታታኛል።»

እሱ-ግን ካርኒቫል ፈተና አይበገረዉም አይነት ይላል።

ድምፅ

«የፈለገዉ ይሁን።የካርኒቫል በአለተኛ ምንጊዜም በአሉን ያከብራል።»

ዘንድሮ ግን እንደምን ጊዜዉም የሚከበር አይነት አልሆነም።የምጣኔ ሐብቱ ድቀት የሁሉንም ቤት እያንኳኳ ነዉ።በአለተኛዉ ለራሱ፥ ለልጅ-ቤተሰቦቹ ያሻዉንና የሚሽቱን በሚፈልጉት መጠን መግዛት አይችልም።ማዘጋጃ ቤቶች፥ ኩባንዮች፥ መስሪያ ቤቶች ለድግሱ የሚያወጡት ገንዘብ መጠን ቀንሰዋል።

ኑሮ-በአለተኛዉን ወገቡን ጠበቅ፥ከወጪዉ ጠንቀቅ ቢያደርገዉም እስከሮብ-እንደ ጠጣ፥ እንደ ጨፈረ፥ እንዳዜመ ይቀጥላል።ግሪኩ፥ላቲኑ፥ ኢጣሊያዉ እንደሚለዉ ካርኒቫል-የሥጋ መሰነባቸነዉ።ከሮብ ጀምሮ ፆም ነዉና።

ZPR Ö-Töne, Agenturen

NM, aa/