የካርቦን ንግድ | ጤና እና አካባቢ | DW | 28.06.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ጤና እና አካባቢ

የካርቦን ንግድ

ከሰሃራ በስተደቡብ የሚገኙ ሃገራት በጽዱ የልማት ስልት የሚኖራቸዉ ተሳትፎ ከፍ እንዲል ናይሮቢ ላይ በጎርጎሪዮሳዊዉ 2006ዓ,ም በተመድ መርሃግብር ተነድፏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:44

ሙቀት አማቂ ጋዞች

መርሃግብሩ ሃገራቱ የልማታቸዉን መሠረት ከባቢ አየርን የማይጎዱ ጽዱ የኃይል ምንጮች ላይ መሠረት አድርገዉ፤ የደን ልማታቸዉን እንዲያሳድጉ የሚያበረታቱ ፕሮጀክቶች በየደረጃዉ እንዲዘጋጁ ያበረታታል። ስምንተኛዉን የአፍሪቃ የካርቦን ጉባኤ ከዛሬ ጀምራ ለቀጣይ ሦስት ቀናት የምታስተናግደዉ ሩዋንዳ ከባቢ አየርን የሚበልክሉ ጋዞችን ልቀት ለመቀነስ የምታደርገዉ ጥረት ትኩረት የሚስብ መሆኑ ይነገርላታል።

ምንም እንኳን ከእሷ በፊት የመጀመሪያዉን ተመሳሳይ ጉባኤ ሴኔጋል፤ ሁለተኛዉን ኬንያ፤ ሦስተኛዉን ሞሮኮ፤ አራተኛዉን ኢትዮጵያ፤ አምስተኛዉን ኮት ዴቩዋር፣ ስድስተኛዉን ናሚቢያ እንዲሁም ሰባተኛዉን ሞሮኮ ቢያስተናግዱም፤ ለስምንተኛዉ የካርቦን ጉባኤ አስተናጋጅነት ሩዋንዳ የተመረጠችዉ ለአካባቢ ጥበቃ የምታደርገዉ ጥረት እና የአየር ንብረት ለዉጥን በመግታት ረገድ የምታሳየዉ እንቅስቃሴ ከግምት ገብቶ መሆኑ ተነግሮላታል። የተመ የአየር ንብረት ለዉጥ ተከታታይ መድረክ UNNFCC ከሩዋንዳ ሪፑብሊክ የአካባቢ አስተዳደር ባለስልጣን ጋር በመተባበር የሚያካሂደዉ የሦስት ቀናት የካርቦን መድረክም ኪጋሊ አዉቶሞቢሎች የሚያስከትሉትን ብክለት ጨምሮ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ የምትወስዳቸዉን ርምጃዎች እና ጥረት ለሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ጋር የምታጋራበት አጋጣሚም ነዉ ተብሏል። በዚህ ጉባኤም ከ600 የሚበልጡ ጉዳዩን በቅርበት የሚያዉቁ ባለሙያዎች ይሳተፋሉ። ስለካርቦን ልቀትና ቅነሳዉ ሲነገር በተለይ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሃገራት ቀደም ብለዉ ያደረሱት እና አሁንም የሚያደርሱት የከባቢ አየር ብክለት ያስከተለዉን የአየር ንብረት ለዉጥ ለመግታት በሃገራት መካከል እንዲካሄድ በኪዮቶ ስምምነት ላይ በንጹህ ልማት ስልት በአማራጭነት የተጠቀሰዉ የካርቦን ንግድ ይነሳል። ይህ እንዴት ይከናወል? ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic