የኪቤራ ማሻሻያ ዕቅድና የነዋሪዎቹ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 23.03.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኪቤራ ማሻሻያ ዕቅድና የነዋሪዎቹ አስተያየት

በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝቦች በተጎሳቆሉ መንደሮች ውስጥ እጅግ አስቸጋሪ ህይወት ነው የሚገፉት ። የቧንቧ ውሀ በሌለበትና ንፅህናውም ባልተጠበቀ አካባቢ የሚኖሩት እነዚህ ድሀ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የጤና ችግሮች የሚሰቃዩ ሲሆን የተፈጥሮ አደጋዎች ሲያጋጥሙም ግንባር ቀደም ተጠቂዎች ናቸው ።

default

የኪቤራ ሕፃናት-በርዳታ ድርጅት ት/ቤት

ይሁንና እነዚህን መንደሮች ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች እንዲህ በቀላሉ የሚሳኩ አይደሉም ። ለምሳሌ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አንድ የድሆች ሰፈርን አፍርሶ የተሻሉ ቤቶች ለመስራት የወጣው ዕቅድ የገጠመው ፈተና በዚህ ረገድ ይጠቀሳል ። በኬንያ መንግስትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደ ሰርቶ ማሳያ የተወሰደው ይህ ዕቅድ ግን በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ በአምነስቲ ኢንተርናሽናል እንደ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው የታየው ።ጉዳዩን የተከታተለችው የዶይቼቬለዋ Antje Diekhans የዘገበችውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ