1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚአፍሪቃ

የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም ፤ ነዋሪዎች

ረቡዕ፣ መስከረም 9 2016

አምስቱ የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ተስፋ እንደተጣለባቸው እና እንደታለመው ከሁለቱ በቀር የተቀሩት የውኃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል። የአካባቢው ማህበረሰብም ከፋብሪካዎቹ አገኛለሁ ብሎ ተስፋ ያደረገው ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እዚህ ግባ አልል ቢለው ምነው ብሎ መጠየቅ ጀምሯል።

https://p.dw.com/p/4WZHV
Afrika | Indigene Völker: Hirtenvolk, Äthiopien
ምስል Joerg Boethling/Imago Images

የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ለአካባቢው ማሕበረሰብ ምን አበርክተው ይኾን?

በኢትዮጵያ የሚሊኒየም መባቻ ኢህአዴግ መራሹ የያኔው የኢትዮጵያ መንግስት «የምዕተ- ዓመቱ የልማት ግቦች ማሳለጫ» ብሎ ሊገነባ ካቀዳቸው በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ናቸው ። በመላው ሀገሪቱ 10 ግዙፍ የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት ሲነሳ አምስቱን የስኳር ፋብሪካዎች በደቡብ ኦሞ ዞን የኦሞ ወንዝ ተፋሰስ አካባቢዎች የሚገኙ ሰፋፊ የሸንኮራ እርሻዎችን ማልማት እንደሚያስችል ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደነበር ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት ። አምስቱ የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች ተስፋ እንደተጣለባቸው እና እንደታለመው  ከሁለቱ በቀር የተቀሩት የውኃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል። የአካባቢው ማህበረሰብም ከፋብሪካዎቹ አገኛለሁ ብሎ ተስፋ ያደረገው ማህበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እዚህ ግባ አልል ቢለው ምነው ብሎ መጠየቅ ጀምሯል። ጤና ይስጥልን አድማጮች ይህ ሳምንታዊው የከኤኮኖሚው ዓለም ዝግጅታችን ነው ።
መሸጋገሪያ 
አምስቱ የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች በደቡብ ኦሞ ዞን ስር በሚገኙ እና አብዛኞቹ አርብቶ አደር የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚኖሩባቸው የኦሞ ወንዝ ተፋሰስ ቆላማ አካባቢዎች እንደመመስረታቸው ከሚኖራቸው ሃገራዊ ፋይዳ በተጨማሪ ለአካባቢው ማህበረሰብ በርካታ ማሕበራዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጠ,ቀሜታዎችን ይዘው ይመጣሉ ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር። እጅግ ኋላ ቀር የሆነ እና ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት ማህበረሰብ እነዚያ ከብቶቹን የሚያሰማራባቸው ሰፋፊ የግጦሽ መስኮች ለሸንኮራ እርሻ ሲውሉ በምትኩ አርብቶ አደሩ ለእርሱና ለቤተሰቡም ሆነ ለሚያረባቸው እንስሳቱ የተሻለ ጊዜ እየመጣለት እንደሆነም ተስፋ አድርጎ ነበር።በኦሞ ስምጥ ሸለቆ የረሀብ አደጋ ስጋት ነገር ግን እንደተባለው ሳይሆን ቀረ። ከአምስቱ የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታቸው ተጠናቆ ከአጠቃላይ የማምረት አቅማቸው በውስን ደረጃ ምርት መስጠት ሲጀምሩ ሦስቱ በጅምር ቀሩ ። ፋብሪካዎቹ ገና ከጅምራቸው ከፊሎቹ በመንግስት በጀት ከፊሎቹ ከውጭ በተገኙ ብድሮች ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ ቢፈስባቸውም እስከዛሬም ግልጽ ባልሆነ ምክንያት የኩራዝ 1 እና 4  የስኳር ፋብሪካዎች በተለያየ የግንባታ ደረጃ ግንባታቸው መቋረጡን ከኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ጠይቀን ተረድተናል። የፋብሪካዎቹ ግንባታ መቋረጥ ከሚኖራቸው ሀገራዊ ኤኮኖሚያዊ ፋይዳ አንጻር ብዙ ማለት ቢቻልም ለዛሬ ጉዳያችን ብለን የተነሳነው ከሁለት ያጣው የአካባቢው ማህበረሰብ ቅሬታ ነው እና ሙሉ ትኩረታችን ወደዚያው እናድርግ። 
በዚሁ የኦሞ ወንዝ ተፋሰስ ቆላማ አካባቢ ኛንጋቶም ወረዳ መቀመጫ ታንጋቴን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የኖሩ እና ስሜ አይጠቀስ ያሉ የመንግስት ሠራተኛ እንደሚሉት ፋብሪካዎቹ ወደ በአካባቢው ለመገንባት ሲወጠኑ ለህብረተሰቡ ይዘው ይመጣሉ የተባለ የልማት ተስፋ ማየት አልተቻለም ይላሉ።በኦሞ ሸለቆ ላይ የተገነቡ የስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የፀጥታ ስጋት 
«ከታቀደለት እሳቤ አንጻር እና መንግስት መጀመሪያ ይህን ሜጋ ፕሮጀክት እየሰራ ባለበት ሰዓት እና ፊት የታቀደው ተግባር ፋብሪካዎቹ ውጤታማ ሆነው ስራ ላይ ወጥተው ብዙ የስራ አጥ ቁጥር ቀንሰው ፣ የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል ብዙ ቃል የተገቡ ነገሮች አሉ ። ነገር ግን በዚያ ልክ እየተኬዱ አይደለም ያለው ።» 
ፋብሪካዎቹ ወደ አካባቢው መምጣታቸው በተለይ ለአርብቶ አደሩ ማህበረሰብ መሰረታዊ የሆኑ እንደ የትምህርት እና የጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ቀዳሚዎቹ እና ተጠባቂ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንደነበሩ እኚሁ ነዋሪ ይናገራሉ። 
«ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ኬላዎች ፣ የተለያዩ የመሰረተ ልማቶች ይሰራሉ ቢባልም መጀመሪያ ላይ የፌዴራሉ መንግስት ያሰራው የመንገድ መሰረተ ልማት ያለበት ከኦሞ ድልድይ መገንጠያ እስከ ፋብሪካው ያለው ነው የተሰራው ። አሁን በስም የምነግርህ ፋብሪካ ቁጥር 2 ፣ 4 ፣ 5 የሚባለው ዝም ብሎ ለስም ነው እንጂ በተግባር የምታየው ነገር አይደለም።»ጀርመናዊትዋ የማኅበረሰብ ጥናት ባለሞያና የሐመር ትዝታዎችዋ
በፋብሪካዎቹ ላይ የሚቀርበው ቅሬታ ከአካባቢው ነዋሪ ባሻገር የክልል ምክር ቤት አባላት ጭምር ጠንከር አድርገው የሚጠይቁት ጉዳያቸው ስለማድረጋቸው ይናገራሉ። አቶ ሎሬ ካኩታ የቀድሞው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል እና የአዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ  ክልል ምክር ቤት አባል ናቸው ። 
ፋብሪካዎቹ እንደተያዘላቸው እቅድ ቢሆን ለውጥ ባመጡ ነበር ይላሉ። 
« በመሰረቱ እንደ እቅዱ እና እንደዓላማው ቢፈጸም ኖሮ ለዚያ ለማህበረሰቡ በጣም ያሻግራል፤ በደንብ አድርጎ ያሻግራል። ለምሳሌ ሰላማጎ ላይ በዐይን ያየነው የነበረው አጠቃላይ የመንግስት ትኩረት ከ2004 ጀምሮ ሰላማጎ ላይ የተሞከሩ ስራዎች አርብቶ አደሮች ፣ አርሶ አደሮች ከፋብሪካው በሚወጡ የተረፈ ምርቶች እንዲጠቀሙ በአይን ለማየት ችለናል። ነገር ግን በኋላ ላይ ቆመ፤ እሱም ሰላማጎ ላይ ብቻ ቆመ ። ወደ ሀመር አልመጣም ፤ ወደ ኛንጋቶም አልመጣም፤ ወደ ዳሰነች አልመጣም ። ኦሞ ወንዝ በሚፈሰው ማለት ነው። ህዝቡ እስካሁን ስኳር ፕሮጀክቱን ይጠብቃል።»
ከኛንጋቶም ወረዳ ተወክለው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት ወ/ሮ ሃና ኤጀም በበኩላቸው ወደ ወረዳቸው የመጣው የስኳር ልማት እርሳቸው የወከሉትን የህብረተሰብ ክፍል መጥቀም ቀርቶ «ለራሱም አልሆነም » ይላሉ ። ከስኳር ፋብሪካው የግንባታ ስራ ጋር ጎን ለጎን መከናወን ሲገባቸው ሳይተገበሩ ለቀሩ የአካባቢው የልማት ስራዎች  ደግሞ የመንግስት ትኩረት ማጣትን በምክንያትንነት ያነሳሉ።
« በስኳር ምክናንያት እንግዲህ አንደኛ ተጠቃሚ የነበረው የናንጋቶም ብሔር ነበር። የስኳር ፕሮጀክት እስካሁን ድረስ ባለፈው ስራ እንደጀመረ ቆሟል። እስካሁን ድረስ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። እንኳን ለህብረተሰቡ ራሱን እንኳ ችሎ እንደ ፕሮጀክት ስራዎች እየተሰሩ አይደለም። ስለዚህ ያኔ ተብሎ ነበረ፤ ግን እስካሁን ድረስ የተደረገ ነገር የለም እና ችግሩ ምን እንደሆነ ፤ ያው እንግዲህ ሁሌ በሚዲያ እንሰማለን ። ስለዚህ ይሄን ጉዳይ እንግዲህ መንግስትም ትኩረት ቢሰጥ ይሄ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ይሆን ነበር። »በኦሞ ዞን ያልታወቀ የአህያ በሽታ ወረርሽኝ ተቀሰቀሰ
ቀደም ሲል የሀገሪቱን የስኳር ፋብሪካዎች በአንድነት ያስተዳድር የነበረው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ፈርሶ የሚንስትሮች ምክር ቤት በ2014 ዓ.ም ባወጣው አዲስ ደንብ እነዚሁ የስኳር ፋብሪካዎች ከፊሎቹ ራስ ገዝ እንዲሆኑ ተደርገዋል። ከፊሎቹ በምክር ቤቱ አዲሱ ደንብ መሰረት በተቋቋመው የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ በተባለ የንግድ ተቋም እንዲተዳደሩ መደረጉን ከተቋሙ የመረጃ ምንጭ ተረድተናል። በዚህ መሰረት ወንጂ/ሸዋ፣ መተሐራ፣ ከሰም፣ ፊንጫኣ እና ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካዎች ራስ ገዝ ፤ እንዲሁም ግንባታቸው የተቋረጠውን የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎችን ጨምሮ ግንባታቸው ተጠናቆ ወደ ማምረት የተሸጋገሩ  የኦሞ ኩራዝ ሁለት እና ሦስት ፋብሪካዎችን እንዲሁም የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካን የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ያስተዳድራቸዋል። 
የኢትዮጵያ መንግስት በራስ አቅም እንዲሁም በብድር ባገኘው ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በአንድ ጊዜ በርካታ የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት ሲነሳ በወቅቱ ድጋፍ ነቀፌታን ማስተናገዱ አይዘነጋም ። በተለይ ዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን ፤ ብሎም  ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕውቀት እና የማስፈጸም አቅም ውስንነት ጋር ተዳምሮ በአንድ ጊዜ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማስፈጸም አይቻለውም የሚለው ትችት ጎልቶ ይሰማም ነበር ። የሆነ ሆኖ ቀን ቀንን እየተካ ወራትም ለአመታት ተሸጋግረው አስራዎቹ ዓመታት ሲቆጠሩ ተስፋ የተጣለባቸው እነዚሁ ፕሮጀክቶች በርካታ ቢሊዮን ብሮችን ወስደው እና የሀገርን ሃበኦሞ ሸለቆ ላይ የተገነቡ የስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የፀጥታ ስጋት ብት ለኪሳራ ዳርገው ሲውተረተሩ ይታያሉ። አሁን ከአካባቢው ማህበረሰብ «እንደጠበቅናችሁ አልጠቀመናችሁንም» ትችት እና ቅሬታ መነሻውም ይኸው ሆኗል። 
አቶ ረታ ደመቀ የስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የህዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ዋና ክፍል ኃላፊ ናቸው ። የኩራዝ ሁለት እና 3 የስኳር ፋብሪካዎች ምንም እንኳ በሙሉ አቅማቸው ባይሆንም ስኳር የማምረት ስራ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የተቀሩት ግን በተለያየ የግንባታ ደረጃ ላይ ደርሰው ስለመቆማቸው በማለከል። ኩባንያቸው በርካታ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማታን ገንብቶ ለህብረተሰቡ ማስረከቡን ቢገልጹም አሁን ከህዝብ የሚመጡ ቅሬታዎች መነሻ ግን በተለይ ግንባታቸው ሳይጠናቀቅ ከቀሩ ፋብሪካዎች ጋር እንደሚያያዝ ነው የሚናገሩት ። ርዳታ ለደቡብ ኦሞ ዞን ተፈናቃዮች
«ምናልባት አራቱም ተጠናቀው ቢሆን ኖሮ እና ወደ ስራ ገብተው ቢሆን ኖሮ ባካባቢ ባለው አርብቶአደር ተጠቃሚነት ቁጥሩም ስፋቱም ይቀጥል ነበር ። ግን አጋጣሚ ሆኖ ሁለት ፋብሪካዎች በመቋረጣቸው ምክንያት በሁለቱ ፋብሪካዎች አካባቢ የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል። ለምሳሌ ወደ 59 የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከ2004 ጀምሮ እስከ 2013 ተገንብተው ለወረዳዎች ተሰጥተዋል።»
ከማህበረሰቡም ሆነ ከህዝብ ተወካይ አባላት የሚነሱ የህዝብ ተጠቃሚነት ቅሬታ ከፍ ያለ ቢሆንም የኢንዱስትሪው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው በመቶ ሚሊዮኖች ብር የሚገመት የማህበራዊ ኃላፊነት የመወጣት ስራ መከናወኑን ይገልጻሉ። 
« ለስልጠና እና እገዛ ለማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ለመሰረተ ልማት ወደ 356 ሚሊዮን 942 ሺ 500 ብር በላይ ወጭ ተደርጓል። እነኚህ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ትምህርት ቤቶችን ፣ የሰው እና የእንስሳት ጤና ኬላዎችን ፣ የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት፣ የመጠጥ ውሃ ተቋማት   የቀበሌ እና የኮሚኒቲ ፖሊስንግ ጽ/ቤቶችን ጨምሮ ተገንብተው አገልግሎት የሚሰጡበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው ማለት ነው »የቤት እንስሳቱ የረገፉበትን አርብቶ አደር ማን ይታደገዋል?
የኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች በቁጥር ሁለት እና ሶስት ፋብሪካዎቹ በውስን አቅሙም ቢሆን እየተወተረተረ እንደሚገኝ ከኢንዱስትሪው የህዝብ ግንኙነት መረዳት ችለናል። የግንባታ ስራዎቻቸው የተቋረጠው የኩራዝ አንድ እና አራት ፋብሪካዎች ጉዳይ ዕጣ ፈንታቸው ገና አልለየም። ከህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደተረዳነው ምናልባትም በሽያጭ ለግል ባለሃብቶች ይተላለፉም ይሆናል። ነገር ግን በዚህም አለ በዚያ የአካባቢው ማህበረሰብ ከእነዚሁ ፕሮጀክቶች በሚገባ መጠቀም ይሻል።  የሚጠብቀው፣ ምናልባትም የህብረተሰቡን አኗኗር የሚቀይር የልማት ስራም ይሆናል። 
« ቢያንስ ኑሮውን የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ይቀይራል ፤ በተጨማሪም በትምህርት ፣ በንቃተ ህሊና ሁሉንም ነገር ያቀርባል የሚል አስተሳሰብ ፤ ከዚህም ሌላ የስራ አጥ ቁጥርን ይቀንሳል የሚል ፤ እንኳንስ ከዚህ አካባቢ ከአጎራባች አካባቢዎች የስራ አጦችን ቁጥር ይቀንሳል ተብሎ  ነበር ። ነገር ግን ፋብሪካው እየሰራ ስላልሆነ እንዲህ ነው ለማለት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነው ያለው »
ታምራት ዲንሳ ነኝ ጤና ይስጥልኝ።

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በከፊል
ቀን ቀንን እየተካ ወራትም ለአመታት ተሸጋግረው አስራዎቹ ዓመታት ሲቆጠሩ ተስፋ የተጣለባቸው እነዚሁ ፕሮጀክቶች በርካታ ቢሊዮን ብሮችን ወስደው እና የሀገርን ሃበኦሞ ሸለቆ ላይ የተገነቡ የስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች የፀጥታ ስጋት ብት ለኪሳራ ዳርገው ሲውተረተሩ ይታያሉ። ምስል Xinhua/picture alliance
የፍንጫ ስኳር ፋብሪካ የደህንነት ስጋት አለበት
በተለይ ዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን ፤ ብሎም  ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕውቀት እና የማስፈጸም አቅም ውስንነት ጋር ተዳምሮ በአንድ ጊዜ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማስፈጸም አይቻለውም የሚለው ትችት ጎልቶ ይሰማም ነበር ። ምስል Negassa Dessalegn/DW
የፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ በጸጥታ ስጋት ውስጥ ሆኖ ስራውን እየሰራ መሆኑ ይነገርለታል
የኢትዮጵያ መንግስት በራስ አቅም እንዲሁም በብድር ባገኘው ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ በአንድ ጊዜ በርካታ የስኳር ፋብሪካዎችን ለመገንባት ሲነሳ በወቅቱ ድጋፍ ነቀፌታን ማስተናገዱ አይዘነጋም ። በተለይ ዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን ፤ ብሎም  ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ዕውቀት እና የማስፈጸም አቅም ውስንነት ጋር ተዳምሮ በአንድ ጊዜ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ማስፈጸም አይቻለውም የሚለው ትችት ጎልቶ ይሰማም ነበር ።ምስል Negassa Dessalegn/DW
አስከፊው ድርቅ በአርብቶ አደሩ ህዝብ ላይ አስከፊ ጉዳት አድርሰዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ተፈጥሮ በነበረው የድርቅ አደጋ ተጎጂ ከነበሩት ውስጥ የአርብቶ አደር ህብረተሰብ በዋነናነት ተጠቃሾች ናቸው ምስል Hamar Woreda Government Communication Affairs Office
የደቡብ ኦሞ የህብረተሰብ ክፍል በህብረ ቀለማት አሸብርቀው
በደቡብ ኦሞ የሚኖሩት አርብቶ አደሮች የትምህርት እና የጤና መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ ቆይተዋል።ምስል GTW/imageBROKER/picture alliance
በኦሞ ወንዝ ተፋሰስ የሚኖረው የህብረተሰብ ክፍል ኑሮውን በከብት እርባታ ላይ አድርጓል
በደቡብ ኦሞ የሚገኘው አብዛኛው የህብረተተሰብ ክፍል አርብቶ አደር እንደመሆኑ መጠን ፤ አስፈላጊው የመሰረተ ልማት እንዲሟላለት ሲጠይቅ ቆይቷል።ምስል Hamar Woreda Government Communication Affairs Office
የኦሞ ወንዝ በደቡብ ኦሞ በርካታ ወረዳዎችን አቋርጦ ያልፋል
የኦሞ ወንዝ በደቡብ ኦሞ ዞን ውስጥ ለሚለሙ ሰፋፊ የሸንኮራ እርሻ ልማቶች አይነተኛ አስተዋጽዖ እንዳላቸው ይነገራልምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ታምራት ዲንሳ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ