የከፍተኛ ትምሕርት ፈተና ዝግጅት በኢትዮጵያ  | አፍሪቃ | DW | 01.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የከፍተኛ ትምሕርት ፈተና ዝግጅት በኢትዮጵያ 

የኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ  የቅድመ መሰናዶ ትምሕርት እና የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ማረጋገጪያ  ፈተና  እያዘጋጀ መሆኑን የኤጄንስዉ የህዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሬዲ ሽፋ ለዶይቼ ቬሌ ተናግራዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:58

የፈተና ዝግጅት

ግንቦት 23 ቀን 2009 ዓ/ም ፈተናዉን ለመስጠት ኤጄንስዉ እቅድ መያዙን አቶ ረዲ ገልፀዉ ዝግጅቱም ከተተናቀቀ በዋላ ለፈተናዉ የተመዘገቡት ከ1.2 ሚሊዮን በላይ የ10ኛ ክፍል ተማርዎችና 288,000 የ12ኛ ክፍል ተማርዎች ለፈተናዉ እንደሚቀመጡ አስረድተዋል።

ባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር  ተማርዎችን ወደ ዩኒቬርስት የሚያስገባቸዉ የእንግለዘኛ ፈተና ሾልኮ ወጥቶ በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ መበታኑ ይታወሳል። ይህም ፈተናዉ እንድራዘም አስገድዷል። ጉዳዩ ብዙ ተማርዎችንና ቤቴሴቦቻቸዉን አስኮርፎ ነበር።

ይህ ፈተና አሁንም ሾልኮ እንዳይወጣ መንግስት ስልት መቀየሱን አቶ ሬዲ ይናገራሉ። መንግስት እየተከታተለ ነዉ ያሉትን ስልት ለጥንቃቄ ሲባል መዘርዘር እንደማይፈልጉም ተናግረዋል።

ተማርዎች ፈተናዉን ለመፈተን ዝግጅታችሁ ምን ይመስላል ብለንም በቅርበት ያሉትን ሰዎች አስተያያት ተቀብለን ነበር። በስልጤ ዞን በዋራቤ ከተማ የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነዉ ፋድል መሃመድ ተማሪዉ የአምናዉን ክስተት «ፈርቶ እያጠና» ይገኛል ይላል። መንግስት ማድረግ ያለበትም እንደሚከተለዉ ይገልፀዋል።

በምዕራብ ዋላጋ ነዋሪ ነኝ ያሉን ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ መንግስት ያለዉን ክፍተት መቆጣጠር አለበት፣ ተማርዎቹ እንደ ባለፈዉ ዓመት መጎዳት የለባቸውም ይላሉ።

ይህንንም ጉዳይ በተመለከተ በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ደረ ገፅ ላይ አስተያያታዉን ጠይቀን፣ «ሲጀመር ኢትዮጵያ ወስጥ ስረዐተ-ትምሕርቱ የሞተ ነው»፣ «ተማሪው ፈተናው ይወጣል ብሎ ስለሚጠብቅ እያጠና እይደለም፣ ስለዚህ የ10ኛና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲያጠኑ ምክር መሰጠት አለበት» ሲሉም አስተያየታቸዉን ሰንዝረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈዉ ዓመት የፈተናዉ መሽሎክን ሰበብ በማድረግ ለወራቶች የፌስቡክ፣ የትዊተር፣ የእንስታግራምና የቫይበር  አገልግሎቶችን አቋርጦ እንደነበረ ይታወሳል። በጊዜዉ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ማረጋገጪያ ፈተናዉን ለመፈተን ከተመዘገቡት 254,000 ተማርዎች ዉስጥም 136,000 ተማርዎች የመንግስት ዩኒቨርስትዎች መግባታቸዉን የሐገር ዉስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቦት ነበር።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic