የከንፈር ወዳጅ፣ በገጠሪቷ ኢትዮጽያ | ባህል | DW | 28.08.2007
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

የከንፈር ወዳጅ፣ በገጠሪቷ ኢትዮጽያ

በአገራችን በአንዳንዱ የገጠሩ ክፍል ትዳር ሳይመሰረት በከንፈር ወዳጅነትን ላይ ብቻ የተመሰረተዉን ወዳጅነት የከንፈር ወዳጅ ብለን እንጠራዋለን። አንዲት ሴት ጡትዋ ሲያጎጠጉጥ አንዳንድ የተፈጥሮ ለዉጦች በሰዉነቷ ላይ ሲከሰቱ የከንፈር ወዳጅ ለመያዝ ትሞክራለች። ወንዱም ቢሆን አስራ አምስት እድሜ ሲሞላዉ ጀምሮ ፍቅረኛ ለመያዝ ልቡ ያስባል ወጣት ሲትን ሲያይ ልቡም ደንገጥ ማለት ይጀምራል

default

በምስራቁ የአገራችንን ክልል በሃረርጌ አካባቢ አንድ ጎልማሳ ያፈቀራትን ልጃገረድ ቤተሰቦችዋን አስፈቅዶ ለአንድ ለሊት ወደ ጭፈራ ቦታ ይወስዳታል። ታድያ ጎልማሳዉ ልጃገረዲቱ ክብሩዋን ጠብቃ ከሱ ጋር ጭፈራዋን ጭፈራ ምሽቱን በደስታ አሳልፋና በክብሯን ጠብቃ ወደ ቤተሰቦችዋ እንደሚመልሳት ይተረጋገጠ ነዉ። ባህላዊ ጥበቃ ለልጃገረዲቱ ይደረጋል። ልጃገረዲቷ በሰላም መመለሷም የተረጋገጠ ነዉ። አንድ ነገር ቢደርስባት እንኳ ጎልማሳዉ ከህብረተሰቡ ከአካባቢዉ የተገለለ ይሆናል። እዚህ ላይ ታድያ ፍቅረኛዉ ሌኞ ይባላል፣ ሸጎዩ የሚባለዉ ደግሞ ጎልማሶች የከንፈር ወዳጆቻቸዉን ይዘዉ በአንድ ምሽት ተገናኝተዉ የሚጨፍሩት ጭፈራ ስነ-ስርአት ነዉ። ይህን ይህን ስናይ ታድያ በአገራችን በአንዳንድ ማህበረሰብ ዉስጥ ቤተሰቦች ልጆቻቸዉን ነጻነት የሚሰጡበት ሁኔታ እንዳለ ይታያል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በአንድ ማህበረሰብ ዉስጥ ያለዉን ቁሳዊ ባህል ጥናት ወይም የፎክሎር መምህር አቶ መስፍን መሰለ በቦረና አካባቢ ባለ ማህበረሰብ የከንፈር ወዳጅ ጉዳይ ሰፊ ጥናት አካሂደዋል። በቦረና አንዲት ልጃገረድ እስከ አምስት የከንፈር ወዳጆች ይኖሩዋታል። አብዛኛዉን ግዜ የከንፈር ወዳጃጅ የነበሩ ወጣቶች ለትዳር አይበቁም ......

 • ቀን 28.08.2007
 • አዘጋጅ Azeb Tadesse
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/E0mC
 • ቀን 28.08.2007
 • አዘጋጅ Azeb Tadesse
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/E0mC