የከተማ ወንዞች ልማት ፕሮጀክት በአዲስ አበባ | ኢትዮጵያ | DW | 22.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የከተማ ወንዞች ልማት ፕሮጀክት በአዲስ አበባ

ፕሮጀክቱ በሦስት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሏል። ይህ የወንዞች ልማት ፕሮጀክት የታሰበው አዲስ አበባን አቋርጠው በሚያልፉ በኹለት ታላላቅ ወንዞች አጠቃላይ 27,5 ኪሎ ሜትር ርዝመትን አካልሎ ሊሠራ ነው።

 
2,5 ቢሊየን ብር ይፈጃል የተባለው የአዲስ አበባ ወንዞች የመናፈሻ ልማት ሥራ ፕሮጀክት ትናንት ይፋ ሆኗል። ፕሮጀክቱ በሦስት ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሏል። ይህ የወንዞች ልማት ፕሮጀክት የታሰበው አዲስ አበባን አቋርጠው በሚያልፉ በኹለት ታላላቅ ወንዞች አጠቃላይ 27,5 ኪሎ ሜትር ርዝመትን አካልሎ ሊሠራ ነው። ከከተማዋ ልማት አኳያ ፈጣን ለውጥን የማምጣት ኃይል እንዳለው የተገለፀው ፕሮጀክት ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ የሚዘረጉት ወንዞች ላይ እንደሚተገበር ተገልጿል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ