የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ተቃዉሞ | ኢትዮጵያ | DW | 30.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች ተቃዉሞ

በባህር ዳር ከተማ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ድህንነታችን አደጋ ላይ ነዉ ጥበቃ ይደረግልን ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡ የከባድ መኪና ሹፌሮቹ አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ ሥራ እናቆማለን ሲሉ በያዟቸው መፈክሮች አስጠንቅቀዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:47

ሹፌሮች በማይታወቁ ሰዎች በሚከናዎቻቸዉ ዉስጥ ይገደላሉ


በባህር ዳር ከተማ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ድህንነታችን አደጋ ላይ ነዉ ጥበቃ ይደረግልን ሲሉ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡ የከባድ መኪና ሹፌሮቹ አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጠን ከሆነ ሥራ እናቆማለን ሲሉ በያዟቸው መፈክሮች አስጠንቅቀዋል፡፡ በተለምዶ የተባበሩት ነዳጅ ማደያ እስከ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ድረስ ከ100 በላይ ሹ ፊሮች ተሽከርካሪዎቻቸዉን እየነዱና ጥሩምባ እነፉ ቅሪታና ስሞታቸዉን አሰምተዋል።

የተቃዉሞ ሰልፈኞቹ ባህርዳር በሚገኘዉ ርዕሰ መስተዳድር ህንፃ ከደረሱ በኋላ ደግሞ ከህንፃው ፊትለፊት ቅሪታቸዉን በጩኸት አሰምተዋል። እንድያም ሆኖ ሰልፈኞችን ወጥቶ ያነጋገረ ባለስላጣን አልነበረም፡፡ ጋዜጠኞች የርዕሰ መስተዳድሩን የፀጥታ አማካሪ ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም ጉዳዩ እርሳቸውን እንደማመለከት ተናግረዋል፡፡ በቅርቡ ከሦሰት በላይ አሽከርካሪዎች በማይታወቁ ሰዎች በሚከናዎቻቸዉ ዉስጥ እንደተገደሉና በርካቶች ደግሞ እየታገቱ ከአቅማቸው በላይ ገንዘብ እንደሚጠየቁ አመልክተዋል፡፡


ዓለምነዉ መኮንን


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች