የኦፌኮ ባለሥልጣናት ክስ | ኢትዮጵያ | DW | 26.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኦፌኮ ባለሥልጣናት ክስ

አቶ በቀለ ገርባና ባልደረቦቻቸዉ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ19ኛ የወንጀል ችሎት እንደነገሩት ቤታሰቦቻቸዉ እንዳይጎበኟቸዉ ከልክለዋቸዋል።ጨለማ ቤት ዉስጥ ታስረዋል።ሌላም በደል ተፈፅሞባቸዋል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:28
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:28 ደቂቃ

የኦፌኮ ባለሥልጣናት ክስ

የኢትዮጵያ መንግሥት የአሸባሪነት ክስ የመሠረተባቸዉ የተቃዋሚዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) መሪዎች የታሠሩበት ወሕኒ ቤት መብታቸዉን እንደነፈጋቸዉ፤ እንዲሚያጉላላና ጨለማ ቤት እንዳሰራቸዉ ዛሬ ለቀረቡበት ፍርድ ቤት አመለከቱ።በአቶ ጉርሜሳ አያና መዝገብ የተከሰሱት የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባና ባልደረቦቻቸዉ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለ19ኛ የወንጀል ችሎት እንደነገሩት ቤታሰቦቻቸዉ እንዳይጎበኟቸዉ ከልክለዋቸዋል።ጨለማ ቤት ዉስጥ ታስረዋል።ሌላም በደል ተፈፅሞባቸዋል።ችሎቱ የተከሳሾችን ተቃዉሞ ለመስማት ለግንቦት 3 2008 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የፍርድ ቤቱን ዉሎ ተከታትሎት ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

Audios and videos on the topic