የኦጋዴን ጥቃትና የባለሙያ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 25.04.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኦጋዴን ጥቃትና የባለሙያ አስተያየት

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ONLF) ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደሚንቀሳቀስ ቢታመንም በ1970ዎቹ መጀመሪያ ከተደረገዉ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ጦርነት ወዲሕ የትናንቱን ያህል ከባድ ጥቃት ባካባቢዉ አድርሶ አያዉቅም።ኦስሎ-ኖርዌ የሚኖሩት ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ዩሱፍ ያሲን እንደሚሉት ጥቃቱ ከኢትዮጵያ አልፎ ሶማሊያ ካለዉ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም።አቶ የሱፍን ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።