1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦነግ ውዝግብና የምርጫ ቦርድ ምልከታ

ረቡዕ፣ መስከረም 6 2013

የምርጫ ቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ተወካይ ሶሊያና ሽመልስ ለዶይቼ ቨሌ እንደተናገሩት ቦርዱ በአቶ አራርሶ ቢቂላ በኩል ያለው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ማገዱን የሚገልጽ ደብዳቤ የተላከ ቢሆንም፤ ሥራ አስፈጻሚውን የሚያግድ ደብዳቤ ግን ከሊቀመንበሩ በኩል አልተጻፈለትም።

https://p.dw.com/p/3iYqR
 Logo Oromo Liberation Front

«የኦነግ ውዝግብ»

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች መካከል የተነሳው ውዝግብ በጠቅላላ ጉባኤ የጸደቀ የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሕግን በመንተራስ እልባት እንደሚያገኝ አስታወቀ። የምርጫ ቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ተወካይ ሶሊያና ሽመልስ ለዶይቼ ቨሌ እንደተናገሩት ቦርዱ በአቶ አራርሶ ቢቂላ በኩል ያለው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ማገዱን የሚገልጽ ደብዳቤ የተላከ ቢሆንም፤ ሥራ አስፈጻሚውን የሚያግድ ደብዳቤ ግን ከሊቀመንበሩ በኩል አልተጻፈለትም። ወይዘሪት ሶሊያና አክለውምት በሊቀመንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ ወገን በኩል ለመጨረሻ ጊዜ ለቦርዱ የተጻፈው ደብዳቤ የሐምሌ 19 እና 20፤ 2012 ዓ.ም. ሥራ አስፈጻሚው የታደመበት የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው በግንባሩ ሕግና ቁጥጥር ውድቅ መደረጉን የሚገልጽ ነው። የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወገን ይህን የሕግና ቁጥጥር ኮሚቴ መግለጫን መርህን ያልተከተለ በሚል ያጣጥላል። የሊቀመንበሩ ወገን በበኩሉ የሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴ አባላቱ በፓርቲውም ሆነ በምርጫ ቦርድ በኩል እውቅና የተነፈገ ነው በሚል ያነሳዋል፡፡ ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል፡፡

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ