የኦነግ እና የኦዴፓ ስምምነት  | ኢትዮጵያ | DW | 13.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኦነግ እና የኦዴፓ ስምምነት 

የኮሚቴው ፀሐፊ ለDW እንደተናገሩት ሠራዊቱ ወደ ካምፕ ሲገባም ችግር እንዳይገጥመው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል። የኮሚቴው አባላት ለዚሁ ተግባር ከዛሬ ጀምሮ በ12 ዞኖች ወደሚገኙ 22 ወረዳዎች እንደሚሰማሩ የአባ ገዳዎች ህብረት ተናግሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:26

የኦነግ እና የኦዲፒ ስምምነት 

በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሠራዊት ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ ወደ ጦር ሠፈር (ካምፕ) ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኦሮምያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ የእርቀ ሰላም የቴክኒክ ኮሚቴ አስታወቀ። የኮሚቴው ፀሐፊ ለDW እንደተናገሩት ሠራዊቱ ወደ ካምፕ ሲገባም ችግር እንዳይገጥመው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል። የኮሚቴው አባላት ለዚሁ ተግባር ከዛሬ ጀምሮ በ12 ዞኖች ወደሚገኙ 22 ወረዳዎች እንደሚሰማሩ የአባ ገዳዎች ህብረት ተናግሯል። የኦነግ ሰራዊት ወደ ጦር ሠፈር የሚገባው ትጥቁን ለአባ ገዳዎች በማስረከብ ነው ተብሏል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው።

ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች