የኦነግ ሠራዊት አባላት ጊዜያዊ ካምፕ እየገባ ነው | ኢትዮጵያ | DW | 21.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኦነግ ሠራዊት አባላት ጊዜያዊ ካምፕ እየገባ ነው

ምንም እንኳን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ትጥቅ አንፈታም ያሉ የኦነግ ሠራዊት አባላት አሉ ተብሎ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ቢሰራጭም DW ያነጋገራቸው አባገዳ ግን ትጥቅ አልፈታም ያለ አካል የለም ሲሉ መልሰዋል።

 የኦሮምያ ክላላዊ መንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከዚህ ቀደም በደረሱበት ስምምነት መሠረት ካለፉት 3 ቀናት አንስቶ የኦነግ ሠራዊት አባላት ወደ ተለያዩ ጊዜያዊ ካምፖች እየገቡ ነው። አቀባበልም እየተደረገላቸው ነው። እስካሁን ግን አሉ ከተባሉት የሠራዊት አባላት ግማሽ ያህሉ እንኳን አልተመለሱም ተብሏል። ምንም እንኳን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ትጥቅ አንፈታም ያሉ የኦነግ ሠራዊት አባላት አሉ ተብሎ በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን ቢሰራጭም DW ያነጋገራቸው አባገዳ ግን ትጥቅ አልፈታም ያለ አካል የለም ሲሉ መልሰዋል። ስለ ሂደቱ  የአሶሳውን ዘጋቢያችንን ነጋሳ ደሳለኝን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic