የኦብነግ ወታደሮች በሶማሌላንድ መከበብ | ኢትዮጵያ | DW | 14.09.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኦብነግ ወታደሮች በሶማሌላንድ መከበብ

ሶማሌላንድ ከ250 በላይ የኦብነግ ታጣቂዎችን መክበቧንና 50 ያህሉን መግደሏን አስታውቃለች። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር የኢትዮዽያን መንግስት ለማስደሰት የተቀመረ ፈጠራ ሲል ገልጾታል።

default

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር አባላት እንደሆኑ የታመኑ 250 ታጣቂዎችን በሶማሌላንድ፤ በጅቡቲና በሶማሌላንድ ድንበር ላይ በሚገኝ የሶማሌላንድ ግዛት ውስጥ መክበቧንና ማባረሯን አስታወቀች። የሶማሌላንድ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሞሀመድ ዩሱፍ አዋሌ እንደገለጹት ድንበር አቋርጠው የገቡት ታጣቂዎች በተሰነዘረባቸው ጥቃት ሸሽተው ወደኢትዮዽያ ግዛት ሄደዋል። በዚህ ጥቃት 50 ታጣቂዎች በሶማሌላንድ ኃይል መገደላቸውን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። እነዚህ ታጣቂዎች የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር አባላት ለመሆናቸው ትተው ከሄዷቸው የተለያዩ ማስረጃዎች እንደተረጋገጠ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ክሱን የፈጠራ ሲል አስተባብሏል። የግንባሩ ቃል አቀባይ አብዱራህማን መህዲ የሶማሌላንድ አዲሱ መንግስት ከኢትዮዽያ መንግስት ጋር የገጠመውን ችግር ለመሸፈን ሲል የፈጠረው ክስ ነው ብለዋል።

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች