የኦባማ ጋዜጣዊ መግለጫ | ዓለም | DW | 15.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኦባማ ጋዜጣዊ መግለጫ

ኦባማ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ለሃብታም አሜሪካውያን ያቀዱትን የግብር ጭማሪ ሃገሪቱን ከኤኮኖሚ ውድቀት ለማዳን ሲሉ ሪፐብሊካውያን መቀበል እንዳለባቸውም አሳስበዋል ። ከአጠቃላዩ ህዝብ 2 በመቶ በሚሆኑት አሜሪካውያን የግብር ጭማሪ መደረጉን ሪፐብሊካውያን ይቃወማሉ ።


የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሪፐብሊካውያን እንደሚፈልጉት ለባለሃብቶች የግብር ፋታ እንደማይሰጡ ዳግም አስታወቁ ። ኦባማ ለ 2 ተኛ የሥልጣን ዘመን ከተመረጡ በኋላ ትናንት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለሃብታም አሜሪካውያን ያቀዱትን የግብር ጭማሪ ሃገሪቱን ከኤኮኖሚ ውድቀት ለማዳን ሲሉ ሪፐብሊካውያን መቀበል እንዳለባቸውም አሳስበዋል ። ከአጠቃላዩ ህዝብ 2 በመቶ በሚሆኑት አሜሪካውያን የግብር ጭማሪ መደረጉን ሪፐብሊካውያን ይቃወማሉ ። ኦባማ በትናንቱ ጋዜጣዊ መግለጫቸው በኢኮኖሚ በውጭ ግንኙነት በስደተኞችና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል ። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic