የኦባማ የጋና ጉብኝት | ኢትዮጵያ | DW | 10.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኦባማ የጋና ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጋናን ለመጎብኘት ዛሬ ማታ ርዕሰ ከተማይቱ አክራ ይገባሉ ።

default

የጋና ዋና ከተማ አክራ

ኦባማ የፕሬዝዳንትነቱን መንበር ከተረከቡ ወዲህ ወደ አፍሪቃ ክፍለ ዓለም ጎራ ሲሉ የጋናው ጉብኝታቸው ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ። ከአፍሪቃ ግዙፍ ምጣኔ ሀብት የሚያንቀሳቅሱትን ናይጀሪያ እና ደቡብ አፍሪቃን ወይም የአባታቸውን ሀገር ኬንያን ከመጎብኘት ይልቅ ኦባማ ጋና ለጉብኝት ለምን መረጡ ? ጋናስ ከኦባማ ጉብኝት ምን ታተርፋለች ? ኦባማ በአፍሪቃ የሚያራምዱት አጀንዳስ ምንድ ነው ? ሂሩት መለሰ በነዚህ ጥያቄዎች ላይ የጀርመን ዓለም ዓቀፍ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ጥናት ተቋም ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ እና የምጣኔ ሀብት ምሁር ዶክተር Dirk Kohnert እንዲሁም ጋናዊው የምጣኔ ሀበት ምሁርና ጋዜጠኛ ሞሀመድ ማርዙክ የሰጧቸውን አስተያየቶች ያካተተ ዘገባ አጠናቅራለች ።

ሂሩት መለስ