የኦባማ የኩባ ጉብኝት | ዓለም | DW | 21.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የኦባማ የኩባ ጉብኝት

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በኩባ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸዉ። የእሳቸዉን ጉብኝት አስመልክተዉ የኩባ መገናኛ ብዙሃን ኦባማ ኩባን ከመርገጣቸዉ አስቀድመዉ በሀገሪቱ ለዉጥ ሊመጣ እንደሆነ አስተያየት መሰንዘራቸዉን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:07

ባራክ ኦባማ እና ራውል ካስትሮ

ፕሬዝደንት ኦባማ ቤተሰቦቻቸዉን አስከትለዉ ትናንት ኩባ የገቡት በአሜሪካን እና ኩባ መካከል ከ50 ዓመታት በላይ የተቋረጠዉ ግንኙነት ዓለምን ባስገረመ መንገድ ከአንድ ዓመት በፊት እንደ አዲስ ከተሻሻለ በኋላ ነዉ። ባራክ ኦባማ ከ88ዓመታት ወዲህ ኩባን የጎበኙ የመጀመሪያዉ አሜሪካዊ ፕሬዝደንትም ተብለዋል። የኦባማ ጉብኝት በሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ላይ ምን ያመጣል ብሎ መገመት ይቻል ይሆን? የዋሽንግተን ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴን በዚህ ጉዳይ ላይ በስልክ በአጭሩ አነጋግሬዋለሁ፤

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic