የኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሕዝብ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 24.07.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሕዝብ አስተያየት

ኬንያ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማን ለመቀበል የፀጥታና የደህንነት ይዞታዋን በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከሯ እየተነገረ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:26
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
05:26 ደቂቃ

የሕዝብ አስተያየት

ዋና ዋና መንገዶች ለጊዜዉ እንደሚዘጉ የገለፁት ባለስልጣናት ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያዉም እንዲሁ እሳቸዉን የያዘዉ አዉሮፕላን ሲደርስም ሆነ የኬንያ ጉብኝታቸዉን ፈፅመዉ ወደ ኢትዮጵያ በሚጓዙበት ሰዓትም እንደሚዘጋ ገልጸዋል። ሳፋሪኮም የተሰኘዉ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅትም በኦባማ ቆይታ ወቅት አገልግሎቱ ችግር ሊገጥመዉ እንደሚችል ከወዲሁ ለደንበኞቹ ጠቁሟል። ናይሮቢ ላይ በሚካሄደዉ የንግድ ጉባኤ የሚገኙት ኦባማ እሁድ ዕለት ወደኢትዮጵያ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት አስመልክቶ የሕዝብ አስተያየት አሰባስበናል።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic