የኦባማ ዓመታዊ የመርህ ንግግር | ዓለም | DW | 29.01.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኦባማ ዓመታዊ የመርህ ንግግር

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የያዝነው የጎርጎሮሳውያኑ 2014 ዓም የተግባር ዓመት እንዲሆን ለአሜሪካ ምክር ቤትና ለአሜሪካ ህዝብ ጥሬ አቀረቡ ።

ሥልጣን ከያዙ ጀምሮ የሪፐብሊካኖች ተቃውሞ እቅዳቸውን ለማሳካት እንቅፋት የሆነባቸው ኦባማ ትናንት ማታ ባሰሙት ዓመታዊ የመርህ ንግግራቸው የአሜሪካን ምክር ቤትን ሥልጣን ሳይጠበቁ ሥልጣናቸውን በመጠቀም እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ገልፀዋል ። በንግግራቸው በአሜሪካን ህዝብ መካከል የሚታየውን ሰፋ የገቢ ልዩነት ለማስተካከልና የሠራተኞችንም ዝቅተኛ የክፍያ መጠን ከፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ። ይበልጡን በሃገር ውስጥ ጉዳዮች ላይ ባተኮረው የአንድ ሰዓት ከ 16 ደቂቃ ንግግራቸው ኦባማ የውጭ መርህቸውንም በአጭሩ አሳውቀዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic