የኦባማ እና የነታንያሁ ውይይት | ዓለም | DW | 07.07.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኦባማ እና የነታንያሁ ውይይት

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ነታንያሁ የመከከለኛውን ምስራቅ የሰላም ድርድር በአዲስ መንገድ እንዲጀመር መስማማታቸውን አስታወቁ ።

default

ኦባማ እና ነታንያሁ

ትናንት ዋይት ሀውስ ውስጥ የመከሩት ሁለቱ መሪዎች በእስራኤልና በፍልስጤም መሪዎች መካከል ተከታታይና ቀጥተኛ የሰላም ድርድር እንደሚጀመርም ጠቁመዋል ። ነታንያሁና ኦባማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዚህ ቀደም ቀዝቅዟል የተባለው የእስራኤልና የአሜሪካን ግንኙነት እጅግ ጠንካራ እንደሆነ አስታውቀዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ