የኦባማ እና ሺ-ጂንፒንግ ዉይይት | ዓለም | DW | 10.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኦባማ እና ሺ-ጂንፒንግ ዉይይት

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማና የቻይናው የሥልጣን አቻቸው ሺ-ጂንፒንግ ለመጀመርያ ግዜ በዩናይትድ ስቴትሷ ግዛት ካሊፎርንያ ላይ ተገናኝተዉ ተወያይተዋል።

ሁለቱ መሪዎች ወደ ስምንት ሰዓት በፈጀዉ ዉይይታቸዉ፤ በሃገራቱ መካከል በቀጣይ በሚደርጉት ትብብር መሰረታዊ ነገር ላይ ያተኮረ ሳይሆን እንዳልቀረም ተነግሮአል።
ሁለቱ የመንግስታት መሪዎች ወደ ስምንት ሰዓታት ከፈጀዉ ዉይይታቸዉ በኋላ የተለያዩት በዝምታ ነበር። በዉይይታቸዉ መጨረሻም ሆነ በሽኝት ወቅት አዉሮፕላን ማረፍያ ምንም አይነት ጋዜጣዊ መግለጫን አልሰጡም። በሌላ በኩል የሁለቱን መሪዎች የግንኙነት መቋጫን በማስመልከት ዋይት ሃዉስ አንድ አነስ ያለች ዘገባን አዉጥቶአል። ይኸዉም የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማና የቻይናው የሥልጣን አቻቸው ሺ-ጂንፒንግ በካይ ጋዞችን ለመቀነስ መስማማት ይፈልጋሉ የሚል ነበር።


ሁለቱ የመንግስታት መሪዎች ለስምንት ሰዓታት በምታቃጥለዉ የካሊፎርንያ ፀሃይ፤ ከሎሳንጀለስ 200 ኪሎ ሜትር ግድም ርቀት ላይ በሚገኘዉ የራንቾ ሚሪዥ የተንደላቀቀ ስፍራ ላይ ሲወያዩ፤ ስለ ለአካባቢ አየር ለውጥ ጉዳይ የያዙት ርዕስ ግን፤ የመጀመርያዉ የመወያያ ነጥባቸዉ አልነበረም። ሁለቱ የመንግስታት መሪዎች በአማረዉ የመዝናኛ ፓርክ ሽርሽር እያሉ ስለምን እንደተወያዩ ለማወቅ ምናልባት አበባ ዛፍ ተክሉን መሆን ያስመኛል። በርግጥም የተወያዩት በመረሃ ግብራቸዉ ቅድምያ የሰጡትን ርዕስ ብቻ መሆን አለበት፤ ስለ ስለላ ጉዳይ ለምሳሌ። እንደሚታወቀዉ ዩኤስ አሜሪካ ስለ ወታደራዊ ስልት ጉዳይ እና ስለ ኢንዱስትሪ ምስጢር፤ ቻይና በኢንተርኔት በኩል ፈልፍላ አይታለች ስትል፤ በተደጋጋሚ ከሳታለች። በዚህ ጉዳይ ዙርያ ፕሪዚደንት ኦባማ፤ ቀደም ሲል በአንድ ጉባኤ የእረፍት ሰዓት ወቅት እንዲህ ሲሉ ተናግረዉ ነበር፤
«ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይና የኢንተርኔት ደህንነት ጥበቃ እና የፈጠራ ስራዎች የባለቤትነት መብት ጥበቃን በተመለከተ በጋራ መስራትን ይፈልጋሉ»


እስከ ካሊፎርኒያዉ ዉይይት ድረስ አሜሪካዉያን በኢንተርኔት ስለላ ጉዳይ ቻያይናዉያን ሲወነጅሏቸዉ ቆይተዋል። ባለፉት ቀናት ግን ሁኔታዉ ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆነ። ዩናይትድ ስቴትስ በዓለም ዙርያ ከሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መረጃን በመሰብቧ፤ ከፍተኛ ሂስ ላይ ወደቀች። በሌላ በኩል የአሜሪካኑ ዕለታዊ ጋዜጣ ዋሽንግተን ፖስት ፕሪዚደንቱ ለወታደሮች እና ለስለላ ድርጅት ምሁራኖች፤ የሰጡትን ትዕዛዝ ይፍ አደረገ፤ ይኸዉም ኢንተርኔት ላይ ያለማስጠንቀቅያ ጥቅም ላይ የሚዉል የሰዎችን መረጃ የሚሰበስብ እና ጥቃት የሚያደርስ መረሃ ግብር እንዲሰሩ የሚያዝ ነበር። ይህ መረሃ ግብር ግን ቻይናዉያኑን አላስደሰተም።

በሌላ በኩል በሶርያም ሆነ በሰሜን ኮርያ ስላለዉ ሁኔታ ሁለቱ የመንግስታት መሪዎች በካሊፎርኒያዉ ግንኙነታቸዉ ይነጋግሩበት አይነጋገሩበት የተገለጸ ነገር እንብዛም የለም። ምናልባትም የሁለቱ መሪዎች ግንኙነት በይበልጥ ለመግባባት እና ለመዋዋቅ እና ለመተማመን ያደረጉት ይሆናል፤ ፕሪዚደንት ኦባማ ከመጀመርያዉ ሰዓታት ዉይይት በኋላ እንደተናገሩት
« በዓለም ዙርያ በሚከሰት ፈታኝ ሁኔታ ላይ፤ አንድ ላይ የመስራት እና አንድ ላይ የመጣመር ፍላጎታችን የሁለታችንም ፍላጎት ነዉ»
ቻይና እና ዩናይትድ ስቴትስ ገና ያልተፈቱ በርካታ ችግሮች አሏቸዉ። ለምሳሌ በኤኮኖሜ ጉዳይ ዘርፍ ያለዉ ግንኙነታቸዉ፤ የንግድ ዘርፍ ጦርነት በመባል ይታወቃል። በሌላ በኩል ቻይና ፤ አሜሪካ በምዕራብ ፓሲፊክ ሃያል አገር ትሆናለች የሚል ፍራቻ አላት። ፕሪዚደንት ኦባማ በበኩላቸዉ በተደጋጋሚ እንደገለጹት ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ አካባቢ ላይ በኤኮኖሚ እና በወታደራዊ ተግባር ሃያል መሆንን ትሻለች።


የአሜሪካው ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማና የሩቅ ምሥራቁ እንግዳቸው ሺ-ጂንፒንግ፤ በራንቾ ሚራጌ ይፋዊ ግንኙነት በኋላ ከፕሪዚደንት ሺ-ጂንፒንግ እና ባለቤታቸዉ ጋር ሻይ መጠጣታቸዉ ተገልጾአል። የፕሪዚደንት ኦባማ ባለቤት ሜሼል ኦባማ ግን፤ የአሜሪካዉ እና የቻይናዉ የመንግስታት መሪዎች፤ ለሁለት ቀናት የተወያዩበትን የራንቾ ሚሪዥን ስፍራ እጅግ ርቀዉ ነዉ የሰነበቱት።

ሳቢና ፍሪትዝ /አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic