የኦባማ መልዕክት | ዓለም | DW | 13.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የኦባማ መልዕክት

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመናቸው የመጨረሻ የሆነውን የአሜሪካ ሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ንግግር ዩናይትድ ስቴትስ ከዓለም ዋነኛዋ ኃያል ሀገር መሆኗ እንደማያጠያይቅ አመለከቱ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:28
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:28 ደቂቃ

የኦባማ ንግግር

ወሳኝ በሆኑ የዓለም ጉዳዮች ላይም ዩናይትድ ስቴትስ ምክር ከተቀናቃኞቿ ሞስኮ እና ቤጂንግ በላቀ መልኩ ይፈለጋል ያሉት ኦባማ፤ በሽብር ጥቃት ስጋት የገባቸዉ አሜሪካዉያን በሀገራቸዉ የሚታዩ ለዉጦችን እንዲያጣጥሙ አሳስበዋል። ኦባማ በንግግራቸዉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ ብሄራዊ ደህንነት፣ የከባቢ አየር ለውጥ፣ የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ፈጠራ እና የሀገር ውስጥ የፖለቲካ ክፍፍል ላይ ብዙ አተኩረዋል።

ከዚህም ሌላ አሜሪካ የካንሰር በሽታን ሊፈውስ የሚችል ምርምር በማድረግ ላይ መሆኗንም ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ የፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው የእስልምና ሃይማኖት፣ የስደተኞች ጉዳይና የከባቢ አየር ንብረት ለውጥን በሚመለከት የሚያራምዱትን አቋምም ተችተዋል።

እንዲያም ሆኖ የፖለቲካ ተንታኞች ንግግራቸዉ በስልጣን ዘመናቸው ያስመዘገቡትን ድል በማጉላት በ2016ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራት ፓርቲ እጩዎች የህዝብን ትኩረት እንዲያገኙ በማሰብ የተዘጋጀ ነው ብለዉታል። ከሪፐብሊካንም የሰላ ትችት ገጥሞታል። ዝርዝሩን ናትናኤል ወልዴ ክዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic