የኦሮምያና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰላም ጉባዔ ማጠቃለያ | ኢትዮጵያ | DW | 09.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኦሮምያና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰላም ጉባዔ ማጠቃለያ

ቤኒሻንጉልን ከኦሮሚያ ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ካለፈዉ ክረምት ጀምሮ በተደረጉ ግጭቶች በመቶ የሚቆጠር ሰዉ ተገድሏል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተፈናቅሏል። ግጭቱ እንዳይደገም ይረዳሉ የተባሉ ጉባዔና ዉይይቶች በተደጋጋሚ እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በምዕራብ ኦሮምያ አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ለበርካቶች መፈናቀል ምክንያት የሆነዉን ችግር ለመቅረፍ በአሶሳ ከተማ የሁለቱ ክልል ፕሬዚደንቶች ምኒስትሮች ሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት መሪዎች የተሳተፉበት የማጠቃለያ የሰላም ጉባኤ ተካሂዶአል።

በጉባዔዉ ላይ የኦሮምያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ለማ መገርሳን ጨምሮ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚደንት አቶ አሻድሉ ሃሰን እንዲሁም የሠላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ንግግር አድርገዋል። ቤኒሻንጉልን ከኦሮሚያ ጋር በሚያዋስኑ ድንበሮች ካለፈዉ ክረምት ጀምሮ በተደረጉ ግጭቶች በመቶ የሚቆጠር ሰዉ ተገድሏል፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ተፈናቅሏል። ግጭቱ እንዳይደገም ይረዳሉ የተባሉ ጉባዔና ዉይይቶች በተደጋጋሚ እየተደረጉ መሆኑ ይታወቃል። በጉባዔዉ ላይ የተገኘዉ የአሶሳዉ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።


ነጋሳ ደሳለኝ 


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ       

Audios and videos on the topic