1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ እና ዘላቂ መፍትሄው

ሐሙስ፣ መስከረም 23 2017

የኦሮሚያ ክልል ግጭት የሰላም እልባት ርቆት ለረጅም ጊዜ የቆየ እንደመሆኑ በእጅጉ መወሳሰቡ ነው የሚነሳው፡፡ መንግስት ለግጭቱ የሰላም እልባት እንዲፈልግ ተደጋጋሚ ጥያቄ በሚቀርብለት ባሁን ወቅት በርካታ ታጣቂዎች በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ትጥቅ አውርደው ወደ ስልጠና እየገቡ ነው ይላል፡፡

https://p.dw.com/p/4lNKY
Nord-Shoa-Gemeinde ruft zum Frieden auf / Addis Ababa
ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ የጸጥታ ሁኔታ ዘላቂ መፍትሄ ያገኝ ይሆን ?

የኦሮሚያ ሰላም እና ዘላቂ መፍትሄው 

የኦሮሚያ ክልል ግጭት የሰላም እልባት ርቆት ለረጅም ጊዜ የቆየ እንደመሆኑ በእጅጉ መወሳሰቡ ነው የሚነሳው፡፡

መንግስት ለግጭቱ የሰላም እልባት እንዲፈልግ ተደጋጋሚ ጥያቄ በሚቀርብለት ባሁን ወቅት በርካታ ታጣቂዎች በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ትጥቅ አውርደው ወደ ስልጠና እየገቡ ነው ይላል፡፡

ዘላቂ እልባት የሚያሳስበው የክልል ማህበረሰብ ግን በየጊዜው በሚፈጠር የእንቅስቃሴ ስጋቶች ብሎም እገታ እና የደህንነት ስጋት መፈተኑ አለመቆሙን ያነሳል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ በያመቱ በነቂስ ወጥቶ የሚያከብረው የኢሬቻ ዓመታዊ ክብረ በዓል የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ እንዲሁም በቢሾፍቱ ከተማ በዋናነት የክልሉን ህዝብ ያለ ሃይማኖትና ፖለቲካ ልዩነት አንድ ላይ አሰባስቦ እንደሚውል ይጠበቃል፡፡ ይህንን የኦሮሞ ህዝብ የአደባባይ በዓልን ምክንያት በማድረግ አስቀድሞበፖለቲከኞች እና ከፖለቲካ ውጪም ባሉ ኢሬቻ በአንድነት ስከበር በክልሉ አንድነትና ሰላም የማምጣት ምልክትም ሆኖ ሊሆን ይገባል የሚሉ ጥሪዎች ይቀርባሉ፡፡

የመስቀል በዓል አከባበር እና ወቅታዊ የጸጥታ ተግዳሮት በኦሮሚያ

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ ባለስልጣን ፖለቲከኛ ሙላቱ ገመቹ ግን ሰላም በአንዴ የሚመጣና በአንድ ሁነት የሚጠነሰስ ሳይሆን ከስር መሰረቱ በመስራት የሚመጣ ነው ይላሉ፡፡ አቶ ሙላቱ “ህዝቦችን ከቦታ ቦታ በነጻነት ማንቀሳቀስ ብሎም የመናገርና ሌሎችም መብቶቻቸውን ሚያከብርላቸውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባት፤ አሁን ላላው ግጭትም እልባት ስፈለግ ለሰላም መንገድ መጥረግ በሚቻል መልኩ ሊሆን የሚገባው ነው” ይላሉ፡፡

Äthiopien | Stadt Bishoftu
የቢሾፍቱ ከተማ ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቀበሌ ደረጃ ያዋቀረው አዲስ መዋቅር

የኦነግ-ኦነሰ አመራሮች ውዝግብ አንድምታ

በኦሮሚያ ውስጥ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ-ኦነሰ) በሚል ታጥቆ መንግስትን የሚቃወምና የሚወጋው ሃይል ከዚህ በፊት የተጀመሩት የሰላም ድርድሮች ለመጨንገፋቸው የሰጥቶ መቀበል የድርድር መርህ አልተዘጋጀም ለውን መንግስትን ተወቃሽ ያደርገዋል፡፡ መንግስት በፊናው ታጣቂ ቡድኑን ባልተገተደበ ፍላጎት ማንጸባረቅ ከሷል፡፡

ከሰሞኑ ደግሞ የታጣቂ ቡድኑ መካከል ልዩነቶች ሰፍቶ ውዝግቦች መነሳታቸው ተዘግቧል፡፡ ቢቢሲ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እንደዘገበው የኦነግ-ኦነሰ ማዕከላዊ ኦሮሚያ አዛዥ የሆኑት ጃል ሰኚ ነጋሳ በተባሉትና የቡድኑ ዋና አዛዥ ኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) መካከል እየሰፋ የመጣው ውዝግብ በመካረር ወደ ልዩነት አምርቷል፡፡ ቢቢሲ የኦነግ-ኦነሰ ማዕከላዊ አዛዥ ጃር ሰኚን አነጋግሮ ይህንኑን ማረጋገጡንም በዘገባው ጠቁሟል፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ እና የጸጥታ ትኩረቱ

በርግጥ የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃሉ አዱኛ ከዚህ በፊት ለዶይቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት ይህን ነጥብ አንስተው ነበር፡፡  “በርካታ ቡድኑን የተቀላቀሉ ወጣቶች እየተመለሱ ይገኛሉ፤ አሸባሪ ቡድኑ እርሰ በራሱ እየተቷከሰም ስለሆነ መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማስከበር ኃላፊነቱን ይወጣልም” ነበር ያሉት፡፡

ዘላቂው እልባት

የኦሮሚያና ኦሮሞን ጉዳይ በቅርበት በመከታተል አስተያየት በመስጠት የሚታወቁት የህግ ባለሙያው ዶ/ር ሔኖክ ገቢሳ ግን የተወሳሰበ ያሉት የኦሮሚያ ክልልም ሆነ አጠቃላይ የአገሪቱን ችግር ዘላቂ እልባት መስጠት በፖለቲካው ላይ አስልቶ በመስራት ነው፡፡ “የዚያ አገር ጉዳይ እስካሁን በምርጫ አልሆነም፤ ወደፊትም የሚሆን አይመስልም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ፍላጎታቸው ፈጽሞ የማይገናኝ እና አገራዊ ራዕያቸው የሚጣረዝ ቡድኖች በስፋት በዚያ አገር ተፈጥሯል፡፡ ይህ ደግሞ አንዱ ቡድን በአጋጣሚ ስልጣን ላይ ብወጣ እንኳ ሌላው በመቀናቀን ሰላም የሚያሳጣ ሊሆን ይችላል፡፡ እናም ከምርጫ ይልቅ ስርዓታዊ እና ህገመንግስታዊም ጭምር ለውጥ የሚያመጣው የጠረጰዛ ዙሪያ ውይይት የግድ ያስፈልጋል” ነው ያሉት፡፡

የኦሮሚያ ክልል አሁናዊ የጸጥታ ይዞታና የህብረተሰብ ፍላጎት

የኦሮሚያው ግጭት ከተከሰተ ድፍን ስድስት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት አንዱ ሌላው ተፋላሚ ላይ ብዝትም ዘላቂ እልባትን ማምጣት ግን ቀላል ልሆን አልቻለም፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ