የኦሮሚያ ወጣቶች ተቃዉሞና መድረክ | ኢትዮጵያ | DW | 16.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኦሮሚያ ወጣቶች ተቃዉሞና መድረክ

የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሰባሰበዉ መድረክ ዛሬ ባወጣዉ በመግለጫዉ የአዲስ አበባን የማስፋፋት ዕቅድ «ሕገ-ወጥ» በማለት ተቃዉሞታል። ዕቅዱን በሚቃወሙ ወገኖች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይላት በወሰዱት እርምጃ በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላሳ በላይ ሰዎች መገደላቸዉን፤ በመቶ የሚቆጠሩ መቁሠላቸዉንም መድረክ አስታዉቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:24

የኦሮሚያ ወጣቶች ተቃዉሞና መድረክ

የኢትዮጵያ መንግሥት ለአዲስ አበባ ከተማ የነደፈዉን የማስፋፊያ ዕቅድ በተቃወሙ ሰዎች ላይ የሚወስደዉን የኃይል እርምጃ የኢትዮጵያ ፌደራዊ

ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) አወገዘ። የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሰባሰበዉ መድረክ ዛሬ ባወጣዉ በመግለጫዉ የአዲስ አበባን የማስፋፋት ዕቅድ «ሕገ-ወጥ» በማለት ተቃዉሞታል። ዕቅዱን በሚቃወሙ ወገኖች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ሐይላት በወሰዱት እርምጃ በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላሳ በላይ ሰዎች መገደላቸዉን፤ በመቶ የሚቆጠሩ መቁሠላቸዉንም መድረክ አስታዉቋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ መግለጫዉን ተከታትሎ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ

Audios and videos on the topic