የኦሮሚያ ክልልና የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን መፋጠጥ  | ኢትዮጵያ | DW | 23.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የኦሮሚያ ክልልና የአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን መፋጠጥ 

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ታቃዉሞዎች እንደቀጠሉ ነው። መንግሥት «ፀረ ሰላም ኃይሎች» ያላቸው ወገኖች ተቃዉሞዉን ወደ ብጥብጥ እንደለወጡት ተናግሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:19
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:19 ደቂቃ

ተቃዉሞና ግጭት በኦሮሚያ

ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ/ም በቡኖ-በዳሌ ዞን ጮራና ዴጋ ወረዳዎች ተቃዉሞ እንደነበረና በተከሰተዉ ግጭት የሰዎች ህወት ማለፉን ይታወሳል።  ግጭቱ መከሰቱን ዛሬ በስልክ ያነጋገርናቸው የክልሉ የኮሙኒኬሼን አለፊ አቶ አዲሱ አረጋ አረጋግጠው፣ በተጠቀሰዉ ቀን ከኢትዮጵያ-ሶማሌ የተፈናቀሉ ሰዎች ላይ እየደረሰ ያለዉ ነገር ተገቢነት ብለዋል። ተቃዉሞ በተካሄደባቸው ቦታ የሚኖሩ ሰዎች የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን እና በአስተዳደሮች ላይ ያላቸዉን ብሶት መግለፃቸዉን አቶ አዲሱ ጠቅሰዋል።

ግጭቱን የክልሉ መንግስት፣ ፖሊስ፣ የአካባቢዉ ሽማግለዎችና ፎሌዎች ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ግጭቱን አነሳስተዋል፣ አደራጅተዋል የተባሉት በዞኑ ብቻ 43 ሰዉ መታሰራቸዉን አቶ አዲሱ አክለው ገልጸዋል። ይህ ሆኖ እያለ በአገር ዉስጥ ያሉ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን ግጭቱን የሚያባብስ ዘገባ አቅርበዋል በማለትም አቶ አዲሱ ወቅሰዋል።

በኢ/ኤን/ኤን ላይ አቶ አዲሱ የሰነዘሩትን ወቀሳ እንዲሁም በዘገባቸዉ ላይ ስለግጭቱ ስለተጠቀሙበት ፎቶግራፍ አስተያየታቸዉን ለማግኘት ደጋግመን ብንደውልላቸውም ልናገናቸዉ አልቻልንም።

የዛሚ 90.7 ራዲዮ የጋዜጠኞች ክብ ጠሬጴዛ በሚ,ዉ ዝግጅት «የክልሉ መንግሥት በተከሰተዉ ግጭት ላይ አፋጣኝ ርምጃ አልወሰደም፣ የፌደራል መንግሥት በክልሉ ግጭት እንዳይከሰት ያስተላለፈዉ መመሪያ አልተከበረም፣ የቀድሞ የአገሪቱ አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ያደረጉት የሥራ መልቀቂያ ንግግር «ኃላፊነት የጎደለው፣ ስሜት ነክ» በመሆኑ ለአመፅ ግብዓት ሆኗል፣ የክልሉ ጋዜጠኞች መረጃ እንዳያወጡ በፕሮፖጋንዳ እየተቀጠቀጡ ይገኛሉ» የሚሉ ነጥቦችን አስተናግደዋል።

የጣብያዉ ሥራ አስኪያጅና ጋዜጠኛ ሚሚ ስበሀቱ በዝግጅቱ ላይ በክልሉ ስለታየው ግጭት፣ ክልሉም ሆነ የፌደራል መንግሥት ምን ማድረግ አለባቸው በሚለዉ ሃሳብ ላይ ውይይት እንደተካሄደ  ዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። በአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት እንደማይከበር፣ ጋዜጠኞች እንደሚታሰሩና እንደሚሸማቀቁ የነፍሪደም ሃዉስ እና ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች በየጊዜዉ የሚያወጧቸዉ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ይሁን እንጅ፣ በዝግጅቱ ሃሳብን በነፃ የመግለፅ እና በመረጃ ነፃነት ሕግ ማዕቀፍ ዉስጥ እንደተሠራ ጋዜጠኛዉ ሚሚ ይናገራሉ።

ጋዝጤኛ ሚሚ የአቶ አዲሱ ንግግር ግላዊ አስተያያት እንደሆነና ሚድያዉን (መገኛኛ ብዙሃንን) ለማሸማቀቅ የተደረገ ነዉ ብለዋል።

ባለፈዉ ዓመት በኦሮሚያ ዉስጥ በነበረዉ ተቃዉሞ ዛሚ FM ያሰራጨዉ መረጃ ስህተት ነዉ በማለት የክልሉ ከፍተኛ ባለስጣናት፣ አቶ አባዱላን ጨምሮ፣ በጣብያዉ ላይ ትችት ሰንዝረዉ  እንደነበር ይታወሳል።

መርጋ ዮናስ

አርያም ተክሌ


 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች