የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች ግጭት የምርመራ ውጤት   | አፍሪቃ | DW | 18.10.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች ግጭት የምርመራ ውጤት  

በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች በሚያዋስኗቸው ወረዳዎች የተቀሰቀሰው ግጭት  ብዙ መፈናቀል ማስከተሉን  የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:05
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:05 ደቂቃ

የኦሮሚያ እና የሶማሌ ክልሎች ግጭት ሰለባዎች

የመፈናቀል እጣ የገጠማቸውን ዜጎች ለመርዳት በክልል እና በፌዴራል በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩን ሚንስትሩ አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በግጭቱ  በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ለደረሰው ጥፋት እና ጉዳት ተጠያቂ የሆኑት የፀጥታ ኃይላት እንደሚታወቁ ዶክተር ነገሪ ተናግረው፣ በነዚህ ወገኖች ላይ ስለሚወሰደው ርምጃ ጉዳዩን የማጣራት ስራ እንዳበቃ ወደፊት እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic