የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ረቂቅን የተመለከቱ አስተያየቶች  | ኢትዮጵያ | DW | 04.07.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ረቂቅን የተመለከቱ አስተያየቶች 

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የኢትዮጵያ የሚንስትሮች ምክር ቤት ያፀደቀዉን አዋጅ የኦሮሞ ዲሞክራስያዊ ግንባር ተቃወመ። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሊንጮ ለታ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዓላማ ሌላ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:46

«የመግለጫዉ ጽንሰ ኃሳብ የኦሮሞዎችን ጥቅም የሚያነፀባርቅ አይደለም» አስተያየት


ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የኢትዮጵያ የሚንስትሮች ምክር ቤት ያፀደቀዉን አዋጅ የኦሮሞ ዲሞክራስያዊ ግንባር ተቃወመ። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ሊንጮ ለታ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሌላ መልኩ ሥራ ላይ ለማዋል እና ማኅበረሰቡን ለማጋጨት የታለመ ሊሆን ይችላል። የአፍሪቃ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ሊግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጋሩማ በቀለ ጋሩሳ በበኩላቸዉ የመግለጫዉ ጽንሰ ኃሳብ ኦሮሞዎች በአዲስ አበባ ላይ ያላቸዉን ጥቅም የሚያነፀባርቅ ሆኖ እንዳላገኙት ነዉ የገለፁት ።  አቶ ሌንጮ ለታንና አቶ ጋሩማ በቀለን ያነጋገረዉ የዋሽንግተኑ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባዉን ልኮልናል።  


መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለስ

Audios and videos on the topic