የኦሎፍ ፓልመ ሽልማት ለኮንጎ ዶክተር | ጤና እና አካባቢ | DW | 03.02.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የኦሎፍ ፓልመ ሽልማት ለኮንጎ ዶክተር

በዴምክራቲክ ኮንጎ ተገደዉ የሚደፈሩ ሴቶች በስለት ወይ በጥይት ተጨማሪ ጉዳት በሆዳቸዉ የታችኛዉ ክፍል ላይ ይፈፀምባቸዋል።

...ሕፃኗ ሕፃን አዝላ...

...ሕፃኗ ሕፃን አዝላ...

የጥቃቱ ዓይነት እንደ አማፅያኑ ስልት ይለያያል። የዚህ ዓይነቱ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች የህክም እርዳታ የሚያደርገዉ ሃኪም ቤት ከአስር ሺ በላይ ለሆኑት ህክምና አድርጓል። ሃኪም ቤቱን በማቋቋም ይህክምና ርዳታዉን እየሰጡ የሚገኙት ኮንጓዊዉ ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጌ የጎርጎሮሳዊዉን 2008ዓ,ም የክብር ሽልማት ስዊድን ላይ ተቀብለዋል።