የእግር ኳስ ግጥሚያና ቅሌቱ | ስፖርት | DW | 06.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ስፖርት

የእግር ኳስ ግጥሚያና ቅሌቱ

(ዩሮፖል) እንደሚለዉ የዓለም ተወዳጅ ስፖርት የእግር ኳስ ተጨዋቾች፥ ዳኞች፥ አሠልጣኖች፥ የክለብ ባለቤቶችና ባለሙያዎች ከቅሌት የተነከሩ ናቸዉ።

epa03568018 View of an Europol press conference in The Hague, The Netherlands, 04 February 2013. The European police agency says a wide-ranging match fixing investigation has uncovered more than 380 suspicious matches, including Word Cup and European Championship qualifiers and two Champions League games. EPA/ROBIN VAN LONKHUIJSEN

ዩሮፖል-ጋዜጣዊ መገለጫ


በመላዉ ዓለም በየደረጃዉ ከሚደረጉ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች የአብዛኞቹ ዉጤቶች ከግጥሚያዉ በፊት በቁማርተኞች እንደሚበየን ፖሊስ አጋለጠ።የአዉሮጳ ፖሊስ (ዩሮፖል) እንደሚለዉ የዓለም ተወዳጅ ስፖርት የእግር ኳስ ተጨዋቾች፥ ዳኞች፥ አሠልጣኖች፥ የክለብ ባለቤቶችና ባለሙያዎች ከቅሌት የተነከሩ ናቸዉ።ዩሮፖል ከሲንጋፑር በመላዉ ዓለም የተዘረጋዉን የቁማር መረብ ከሚመሩት ከአንዱ ያገኘዉን መረጃ ጠቅሶ እንዳስታወቀዉ የስድስት መቶ ሰማኒያ ግጥሚያዎችን ዉጤት ከየግጥሚያዎቹ በፊት የወሰኑት በዉርርድ ቁማር የከበሩ ቱጃሮች ናቸዉ።ከስድስት መቶ ሰማንያዎቹ ግጥሚያዎች ሰወስት መቶ ሰማኒያዎቹ አዉሮጳ፥ የተቀሩት አፍሪቃ፥ እስያና ደቡብ አሜሪካ የተደረጉ ናቸዉ።ሥለ ቅሌቱ የበርሊን ወኪላችን ይልማ ሐይለ-ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic