የእጅ ስልክ አገልግሎት፤ በኬንያና ጋና፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 12.09.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የእጅ ስልክ አገልግሎት፤ በኬንያና ጋና፣

በመኖሪያ ቤት ውስጥ ጠቀሜታ የሚሰጥ የስልክ መሥመር ፤ ለአብዛኛው ህዝብ ፈጽሞ ባልተዳረሰበት በአፍሪቃው ክፍለ -ዓለም፤ «ሞባይል» (ተንቀሳቃሽ ወይም የእጅ ስልክ) ያበረከተውና በማበርከት ላይ ያለው ድርሻ በቀላል የሚገመት አይደለም። በተራራ ፣

በሸለቆ ፤ በጫካ ፤ በምድረ በዳ፣ የትም ቦታ ሆኖ ፣ ከዓለም ዙሪያ ፤ በዘመኑ የሥነ ቴክኒክ ፀጋ ፣ ማለትም ፣ በእጅ ስልክ በመታገዝ፤ ፤ መልእክትም ሆነ መረጃ ማግኘትና ማስተላለፍ የተለመደ ጉዳይ ነው። ይኸው ሥነ ቴክኒክ በኬንያና ጋና ሌላም አገልግሎት አለው

በኬንያ፤ ከብሪታንያው የመገናኛ ኩባንያ (ቮዳፎን) ጋር በመተባበር የሚሠራው «ሳፋሪ ኮም» የተባለው፣ የስልክ አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ፣ እ ጎ አ በ 20007 ዓ ም፣ M-Pesa የተሰኘውን መርኀ ግብር ማስተዋወቁ የሚታወስ ነው። M ‚ ሞባይል ለማለት ሲሆን Pesa ደግሞ በኪስዋሂሊ ቋንቋ፣ ጥሬ ገንዘብ ማለት ይሆናል። ስለሆነም፤ በ M- «ፔሳ» መርኀ ግብር አማካኝነት ፤ ገንዘብ በተንቀሳቃሽ ስልክ አማካኝነት እንዲጠራቀምም ሆነ በእጅ ስልክ አጭር መልእክት መላኪያም ሆነ መቀበያ አማካኝነት ፤ ገንዘቡ፣ ከአንዱ ባለእጅ ስልክ ወደ ሌላው ማስተላለፍ ይቻላል ማለት ነው።

ይህ እንግዲህ፣ ልዩ ዓይነት የባንክ አገልግሎት ነው ሊባልም ይችላል። ከኬንያ የዶቸ ቨለ የአፍሪቃው ክፍል ባልደረባ አልፍረድ ኪቲ ያነጋገራቸው ሳሚ ሌዋ የተባሉ ፤ የ M – Pesa መርኀ ግብር ተጠቃሚ ኬንያዊ እንዲህ ይላሉ--

1,«ኑሮዬን በእጅጉ አቅልሎልኛል። አሁን ለወላጆቼ ገንዘንብ እንዲደርሳቸው ማድረግ እችላለሁ። የኤልክትሪክና የውሃ አገልግሎት ክፍያን፤ በትምህርት ቤት ለልጄ የሚከፈል ገንዘብም ለማስተላለፍ አልቸገርም። የሚከፈል የስልክ ግብር ሳይቋረጥ እንዲጠራቀም አድርጋለሁ፤ በከፊልም ለጓደኞቼ እንዲከፍሉ እልክላቸዋሁ።»

ይህን የመሰለ አገልግሎት በመስጠት «አፍሪ ኮም» በጥቂቱ ግብር ያስከፍላል። «ኤም -ፔሣ» ትርፍ የሚያስገኝ ንግድ በማካሄድ በኬንያ ከ 250 ሺ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል ማስገኙቱም ነው የሚነገርለት። የኬንያ ኤኮኖሚ በዚህ ዓይነቱ አሠራር መዳበሩ እንዳልቀረ በመነገር ላይ ሲሆን፤ በተንቀሳቃሽ ስልክ ፤ ገንዘብ ለመላክና ለመቀበል የተሰለፈው ሰው ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱ ነው የተገለጠው። ከናይሮቢ፤ የኤኮኖሚ ባለሙያይቱ ዶ/ር ጆይ ኪሩ ኤኮኖሚው በዚህ ረገድ በቀጣይነት በማደግ ላይ ስለመሆኑ ሲያብራሩ---

2,«(ኤም -ፔሣ) አዎንታዊ ተጽእኖ ነው ያሳረፈው። የፋይናንሱን ዘርፍ ነፍስ ብቻ አይደለም የዘራበት፣ እጅግ እንዲስፋፋም አብቅቷል። ሁለቱም ማለፊያ ነው። «ኤም ፔሣ»፣ በኬንያ በእርግጥ የፋይናንሱን ዘርፍ አጠናክሮታል።»

በ«ኤም ፔሣ » አገልግሎት ሳቢያ የገንዘብ ስርቆት ሥጋት ተወግዷል። በዛ ያሉ ሰዎች በኅብረት በጥቂቱ ገንዘብ እያዋጡ፣ የራሳቸውን ኩባንያ ለማቋቋም መደፋፈራቸው አልቀረም። በአሁኑ ጊዜ 70 ከመቶ ጎልማሶች የሆኑ ኬንያውያን፤ በ M-Pesa ይጠቀማሉ። በ 5 ዓመታት ውስጥ፤ በፋይናንሱ ዘርፍ እጅግ የተሣካ አገልግሎት በመስጠትና በመስፋፋትም የታወቀው ይኸው ድርጅት ሆኗል። በአንዲት በመልማት ላይ በምትገኝ ሀገር እንዲህ ያለ የአገልግሎት ዘርፍ ዕድገት ሲመዘገብ የኬንያው ምናልባት የመጀመሪያው ሳይሆን እንዳልቀረም ነው የሚነገርለት። «ኤም ፔሣ» ያላንዳች ማጋነን፤ የኬንያውያንን ዕለታዊ ኑሮ ለውጦአል። የዩንቨርስቲ ተማሪዋ ጆይስ፤ የኤም ፔሣ ተጠቃሚ ናት።

3,«አጠቃቀሙ ቀላል ነው። ራቅ ካለ ቦታ ፤ እንበል ከአገሪቱ ምዕራባዊ ከፊል ፣ ገንዘብ ሊላክ ይችላል። እናም ናይሮቢ ላይ ተቀምጠህ ፣ በቀጥታ ገንዘቡን ማግኘት ትችላለህ!»

በ« M- ፔሣ» እንደሚታየው ቀልጣፋ አሠራር ፤ በመደበኛ ባንክ ፈጽሞ የሚታሰብ አይይደለም። ጆይስ እንደምትለው፣ ሰው በዚያ ገንዘብ ለመላክም ሆነ ለመቀበል በቀላሉ የማይታሰብ ጊዜ ነው የሚያባክነው። እርግጥ ነው፤ የተጠቀሰው በእጅ ስልክ አገልግሎት መስጫው መርኀ ግብር ፍጹም እንከን የለሽ ነው ለማለት የሚደፍር የለም። ከናይሮቢ ኤልሳቤጥ ማፉራ የተባሉ ወይዘሮ ፤ በመጀመሪያዎቹ ወራት ስላጋጠሙ ችግሮች እንዲህ ያስታውሳሉ።

4,«(ኤም ፔሣ) ሲጀመር ፤ አንዳንድ ችግሮች አጋጥመው ነበር። ለምሳሌ ያህል በስህተት አንድ ቁጥር ከተነካ፣ ገንዘቡ ወዳልተሰብ ሰው ይላካል። ወደ «ሳፋሪ ኮም»፣ ወዲያው ሲደወል ደግሞ፣ ስልክ የሚያነሣ ይጠፋል። አሁን ግን ለደምበኞች አገልግሎት የሚሰጥ ፤ የሚያማክር ክፍል በመኖሩ ፤ ሥራው ያለ እንከን በተቀላጠፋ ሁኔታ በመካናወን ላይ ይገኛል። »

በM-Pesa ፣ ገንዘብ መላክና መቀበል ብቻ ሳይሆን፤ አንዳንድ ኬንያውያን፤ በግል የሂሳብ ደብተር እንደሚደረገው ሁሉ በእጅ ስልክ በተቀየሰው መርኀ-ግብርም ገንዘብ ማጠራቀም ችለዋል። ይህ ደግሞ የሚከናወነው ያላ ባንክ ሂሳብንም ሆነ ሰነድ፤ እንዲሁም ለአገልግሎት በዛ ያለ ክፍያ ሳይጠየቅበት ነው። ይህን ማድረግ የሚቻለው በእርግጥ

« SIM ካርድ »(Subscriber Identity Module) እስካልተለወጠ ድረስ ነው። M –Pesa የተሳካ ውጤት ማስመዝገቡን የተገነዘቡ ሌሎች ኩባንያዎችም ፤ አሁን ወደ ገበያው ብቅ -ብቅ ማለት ጀምረዋል። ለምሳሌ ያህል ፣«ዘይን» የተባለው ኩባንያ፣ Airtel Money ፣ ሌሎች ተፎካካሪዎችም YuCash እንዲሁም Orange Money የሚሰኙ ፣ ተመሳሳይ አገልግሎት እንደሚሰጡ በማስታወቅ ላይ ናቸው። ስለሆነም በኬንያ በአጥጋቢ መልኩ በመከናወን ላይ ያለው ተግባር ፤ በሌላም ሀገር ውስጥ፤ በተለይ በባንክ መደበኛ የሂሳብ ሰነድ የሌላቸው አያሌ ዜጎች ባሉባቸው አገሮች፤ ገንዘብ በእጅ ስልክ አማካኝነት የመላኩና የመቀበሉ ተግባር ስኬታማ እንደሚሆን በሰፊው በመነገር ላይ ነው።

ሱዳን፤፣ ታንዛንያ፤ ህንድና እነዚህን የመሳሰሉ አገሮች፤ ከኬንያው ተመክሮ በአጅጉ ሊጠቀሙ ይችላሉ ነው የሚባለው። አውሮፓ ውስጥ በተለይ በብሪታንያ የተጠቀሰው ዓይነት አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ በመፈተሽ ላይ ነው።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 12.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/167bU
 • ቀን 12.09.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/167bU