የእድገትና ለዉጥ እቅድ | ኤኮኖሚ | DW | 24.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኤኮኖሚ

የእድገትና ለዉጥ እቅድ

እንደ ርእሱ ዐቢይነት ፤ እንዲፈጸም የሚጠበቀው ትግባርም በከፍተኛ ደረጃ የሚተኮርበት ጉዳይ ሊሆን እንደሚገባ ከውጥኑ ሳይታለምበት እንዳልቀረ ይታሰባል። ኢትዮጵያ ፤ የሁለንተናዊ ዕድገትና ለውጥ ተምሳሌት እንድትሆን መመኘት በጎ ነገር ነው። በአቅድ መሠረት መፈጸም ፣ማከናወን መቻሉ ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው።

ከ 80 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላትን፤ በዓለም ውስጥ እጅግ ከደኸዩት አገሮች አንዷ ፣ በመሠረታዊ ልማትም፣ ገና ብዙ የቀራትን ሀገር ፣ በ 5 ዓመት ውስጥ አንድ ከፍ ያለ እመርታ እንድታደርግ ፤ ውጤት ማስገኘት የሚቻልባቸውን ቅድመ ግዴታዎች መርምሮና ግምት ውስጥ አስግብቶ  ለመንቀሳቀስ ማሰብ ፣ ማቀድ   በራሱ አዎንታዊ ነው።
ከ 2002 እስከ 2007 የሚዘልቀው፣ በዋናነት ግብርናና ኢንዱስትሪ ተኮር መሆኑ የሚነገርለት  የኢትዮጵያው  አጠቃላይ የዕድገትና ለውጥ አቅድ   ከ 75-79 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣ ነው የተገመተው። የዕድገትና የለውጥ(ትራንስፎርሜሽን) እቅዱ  ፣ የግማሽ ዘመን(የ 2 ዓመት ከመንፈቅ )ሂደትና ውጤት ፣ ከወዲያኛው ሰሞን  የተገመገመበት የጥናት ውጤት ሲቀርብ፤ ፣ መንግሥት ፣  ምንም እንኳ የኤኮኖሚው ዕድገት እንደታቀደው 11 ከመቶ ሳይሆን በ 8,5 ከመቶ የተወሰነ ሆኖ ቢገኝም፣  ኤኮኖሚው ጠንካራ ነው ሲል  መግለጹ የሚታወስ ነው።
ሙሉ ዉይይቱን ያድምጡ።

ተክሌ የኋላ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic