የእናቶች ቀንና ጤና | ጤና እና አካባቢ | DW | 11.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የእናቶች ቀንና ጤና

የእናቶች ቀን በየዓመቱ በአዉሮጳዉያን የዘመን ቀመር ግንቦት ወር በባተ በሁለተኛዉ እሁድ ይታሰባል።

default

ይህን ዕለት ተመርኩዘዉ የእናቶችን ጤና በሚመለከት የወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት በአሁኑ ወቅት ለእናቶች የተሻለ የጤና ክብካቤ በማድረግ ኖርዌይ አዉስትራሊያን አስከትላ የአንደኛነት ደረጃዉን ይዛለች። ባለፈዉ የአዉሮጳዉያን ዓመት ስዊድን ነበረች የዚህ ክብር ባለቤት። በአንፃሩ አፍጋኒስታንና በርካታ የአፍሪቃ አገራት ለእናቶች ህይወት እንደሌሎቹ ምቹ እንዳልሆኑ ተገልጿል።

በአሜሪካን በእናቶች ቀን የሚደወለዉን ስልክ ያህል ለዘመን መለወጫ እንኳን እንደማያንቃጭል ነዉ አንድ ጥናት ያመለከተዉ። አሜሪካን ዉስጥ የተሰራ አንድ ጥናት እንደሚለዉ ከአገር ዉጭ የሚኖሩ ዜጎች ፓስትካርድም ሆነ አበባ መላክ ቢዘነጉ በዚች ዕለት ስልክ ለየእናቶቻቸዉ መደወልን አያልፏትም። ጥናቱ እንዳመለከተዉም የፍቅረኞች ቀንን ጨምሮ ከሌላዉ ቀን ይልቅ የእናቶች ቀን በርካታ ጥሪዎች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ይስተናገድበታል። ከአገራቸዉ ዉጭ ከሚገኙ ደቡብ አፍሪቃዉያን በዚህ ወቅት ወደአገራቸዉ ለመደወል የስልኩን እጅታ የሚይዙት 91በመቶዉ ይሆናሉ፤ ከእነሱ የሚለጥቁት ጋናዉያን ሲሆኑ 82,7 በመቶ ተመዝግቧል።

Brauchtum global Flash-Galerie

በጥቅሉ ከአንድ እስከአስረኛ ደረጃዉን ከያዙት መካከል፤ ቻይና፤ ካሜሮን፤ ኒዉዚላንድ፤ ጀርመን፤ አዉስትራሊያ፤ ጃፓን፤ ኬንያና ብሪታንያ ይገኛሉ። ግብፅና ኮርያ ደግሞ በዚህ ወቅት ዝቅተኛዉ የስልክ ጥሪ የሚስተናገድባቸዉ አገራት ናቸዉ። በዚህ ዕለት በበርካታ አገራት የሚገኙ እናቶች ከልጆቻቸዉ ከአበባ አንስቶ የተለያዩ ስጦታዎችንና በጭንቅ ወደዚች ዓለም አምጥተዉ በክብካቤ ለማሳደጋቸዉ ምስጋና ይቸራሉ።

ሸዋዬ ለገሠr

ሂሩት መለሰ

ተዛማጅ ዘገባዎች