የእናት ቀን አከባበር | ባህል | DW | 15.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የእናት ቀን አከባበር

በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የዋለዉን የእናቶች ቀን በማስመልከት በርካታ ኢትዮጵያዉን በተለያዩ የማሕበራዊ ደረ-ገፆች እናትን የሚያወድስ እናትን የሚያመሰግን የተለያዩ ስነ-ፅሁፎና ግጥሞች ተለዋዉጠዋል። በተለይ በፊስቡክ ማህበራዊ ድረ መገናኛ ገፅ ላይ የእናቶቻቸዉን ፎቶ ግራፎች በማስቀመጥ እናቶቻቸዉን ያመሰገኑ ኢትዮጵያዉያን እጅግ ብዙ ናቸዉ።

በምዕራቡ ዓለም ሚያዝያ ወር በገባ በሁለተኛዉ ሳምንት እሁድ የእናቶች ቀን በሚል፤ እናትን በማወደስ ለእናት ልዩ ምስጋና በማቅረብ፤ በድምቀት የማክበር፤ የማሰብ ባህልና የተለመደ ነዉ። የእናት ቀን አከባበር መነሻዉ ከዩኤስ አሜሪካ መሆኑና፤ በአሁን ግዜ በበርካታ ሀገሮች ቀኑን የማክበር ባህል መለመዱን ዘገባዎች ያመላክታሉ። የእናቶች ቀን በጀርመን ከጎርጎረሳዉያኑ 1923 ዓ,ም ጀምሮ በየዓመቱ በመከበር ላይ ነዉ። በጀርመን በሥራ ምክንያት ከወላጅ ቤተሰቡ ርቆ የሚኖር ልጅ፤ በእናቶች ቀን፤ ቢቻለዉ እቅፍ አበባን ይዞ እናቱን ለዚህ ስላደረስሽኝ አመሰግንሻለሁ፤ እድሜና ጤና ላንቺ ለእናቴ ክብር ይገባሻል ሲል ለእናት በልዩ ቀን ምስጋና የማቅረብ ባህል የተለመደ ነዉ። በዝያን እለት በተለያዩ አጋጣሚዎች እናቱን በአካል ማግኘት ያልቻለ ደግሞ፤ ስልክ በመደወል ለእናቱ ምስጋናዉና ክብሩን በመግለጽ፤ በዚህም አለ በዝያ፤ በእለቱ በመልክተኛ ለእናቱ እቅፍ አበባ እንዲደርሳት ማድረጉም የተለመደ ነዉ። እናቶችም ታድያ ይህን ቀን በጉጉት ይጠብቁታል። በልጆቻቸዉ ምስጋና እና ክብርም ሲታደሱ ይታያሉ።

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የእናቶች ቀን አከባበር እንዴት ይገልፁታል? ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሰጠኝ ለማግኘት ብዙ ርቄ አልሄድኩም ፤ እናት የምላትን ባልደረባዬን ንጋት ከተማን የእናቶች ቀንን እንዴት አንዳከበረች ጠይቄያት ነበር። እናቴ ከሚሉዋት ሰዎች እንዲሁም፤ ልጆችዋ እቅፍ አበባን እንዳገኘች ገልጻለች። ይህ ባህል በኢትዮጵያም ቢለመድ ምኞትዋ እንደሆነም ሳትገልጽ አላለፈችም። ጀርመን ሃገር ሲኖሩ ከ20 ዓመት በላይ የሆናቸዉን የሁለት ልጆች አባቱ አቶ መስፍን አማረ፤ በቤቴ የእናቶችን ቀን የምናከብረዉ ልጆቼ ለእናታቸዉ የቻሉትን ነገር በማድረግ ፍቅራቸዉን በመግለፅ ነዉ ሲሉ አጫዉተዉናል። ከኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽን ኢኒስፔክተር ግዜሽወርቅ ኃይለማርያም ስለእናት ቀን መከበር ያወቁት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ባገኙት መረጃ ነዉ። እናት ማለት ሁሉ ነገር ነዉ ፤ እናት ማለት ወላጅ እናት፣ እናት ማለት ታጋሽነት፣ እናት ማለት አርበኛ፣ እናት ማለት ሀገር ነዉ ሲሉም ተናግረዋል። በሀገራችን የታወቁ ሴቶችን ክቡር ሥራ በማዉሳት የእናቶች ቀን የማክበር ባህል ቢለመድ ምኞታቸዉ እንደሆንም ገልጸዋል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic