የእነ አቶ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ውሎ | ኢትዮጵያ | DW | 30.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የእነ አቶ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ውሎ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ የወንጀል ችሎት የልደታ ምድብ በነአቶ በቀለ ገርባ ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው የሲዲ ማስረጃ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ እንዲቀርብ ድጋሚ አዘዘ። የትርጉሙን ስራ እንዲያከናውን የታዘዘው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ድጋሚ ትዕዛዝ እንዲጻፍለት ብይን አስተላልፏል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:13

ዓቃቤ ሕግ በነአቶ በቀለ ገርባ ላይያቀረበው የሲዲ ማስረጃ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ እንዲቀርብ ድጋሚ ታዘዘ።

ዓቃቤ ሕግ ይህን ትዕዛዝ አለማክበሩ ስህተት መሆኑን ችሎቱ ዛሬ አስታውቆ፣ ለሚያዝያ ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ተበትኖዋል። የተከሳሽ ጠበቆችም ዓቃቤ ሕግ ስራውን በሚገባ ባለመስራቱ ደንበኞቻቸው ባፋጣኝ ፍትሕ የሚያገኙበትን መብታቸውን ተጋፍቷል ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic