የእነ አቶ ምትኩ በየነ የፍርድ ቤት ውሎ  | ኢትዮጵያ | DW | 18.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የእነ አቶ ምትኩ በየነ የፍርድ ቤት ውሎ 

ከጥረት ኮርፖሬሽን ጋር በተያዘ ተጠርጥረው ጉዳቸው እየተጣራ ያለው የእነ አቶ ምትኩ በየነ የምርመራ ሂደት ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ መታየት ጀምሯል፡፡ አቶ ምትኩ በጠየቁት የዋስትና ጥያቄ ላይና ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጠየቀው ተጨማሪ ቀን ላይ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለነገ ተቀጥሯል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:05

የእነ አቶ ምትኩ በየነ የፍርድ ቤት ውሎ 

አቶ ምትኩ በጠየቁት የዋስትና ጥያቄ ላይና ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በጠየቀው ተጨማሪ ቀን ላይ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለነገ የቀጠረ ሲሆን በሌሎች ተጠርጣሪዎች ላይ 10 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የባሕር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ከሰአት በፊት መጀመሪ የተመለከተው ላፓል የሚባል ካምፓኒ ባለቤት ሆነው ሲሰሩ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ከጥረት ኮርፖሬት ጋር በመመሳጠር የህዝብ ገንዘብ አባክነዋል ባላቸው በእነወ/ሮ አይናለም ኃይለ ልኡልና በሁለት ሴት ልጆቻቸው መዝገብ የተከፈተውን የምርመራ መዝገብ ነው፡፡ የአማራ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ቡድን ባለፉት ቀጠሮ በተሰጠባቸው 14 ቀናት ያከናወነውን ተግባራት ለፍርድ ቤቱ በዝርዝር አቅርቧል፡፡
ሆኖም አንዳንድ የሰነድ ማስረጃዎችን በቀላሉ ማግኘት አልቻልኩም፣ የሰው ምስክሮች አካባቢውን የለቀቁና በተበታተነ ሁኔታ ስለሚገኙ መረጃዎችን አጠናቅቄ አልጨረስኩም በመሆኑም ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቀድልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።


ዓለምነው መኮንን


እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ

 

Audios and videos on the topic