የእስራኤል ፍልስጤም ግጭት | ዓለም | DW | 19.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የእስራኤል ፍልስጤም ግጭት

በምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ አካባቢ አይሁዳዉያን መንፈሳዊ አክብሮት የሚሰጡትን ስፍራ ፍልስጤማዉያን በእሳት መለኮሳቸዉ በሁለቱ መካከል የቀጠለዉን ፍጥጫና ግጭት ሊያባብስ እንደሚችል እየተገለጸ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:56

የእስራኤል ፍልስጤም ግጭት


በሶርያ ኢራቅና የመን እየተካሄደ ባሉት ጦርነቶች ምክንያት ዘመናችን የጦርነት አዉድማ፤ ዋና የስደተኞች ምንጭ የሆነዉ

የመካከለኛዉ ምሥራቅ ቃጣና ከዚህ ወር ጀምሮ ደግሞ የእስራኤል ፍልስጤሞችን ሞትና ቁስለት ሁከት እያስተናገደ ይገኛል። በወሩ መጀመርያ እንደተቀሰቀሰ የሚነገርለት የፍልስጤሞች ተቃዉሞ እንቅስቃሴ ወደሌሎችም እስራኤል ግዛቶች ተስፋፍቶ እስካሁን ከ 40 የሚbmልጡ ወጣት ፍስልሴሞች እንደቀጠፈና ስምንት ወታደሮችን እንደተገደሉ ነዉ የታወቀዉ ። የእለቱ ማሽደረ ዜና ዝግጅት በእስራኤል ፍልስጤም ግጭት ላይ ያተኩራል።
በምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ አካባቢ አይሁዳዉያን መንፈሳዊ አክብሮት የሚሰጡትን ስፍራ ፍልስጤማዉያን በእሳት መለኮሳቸዉ በሁለቱ መካከል የቀጠለዉን ፍጥጫና ግጭት ሊያባብስ እንደሚችል እየተገለጸ ነዉ። ሰሞኑን የተጋጋለዉን የፍልስጤም፤ እስራኤል ግጭት አነሳስተዋል በመባል የሚከሰሱት ፕሬዝደንት ማህሙድ አባስ ድርጊቱን በፍጥነት ኮንነዋል።

በምራባዊ ናብሉስ ግዛት የሚገኘዉ አይሁዶች የዮሴፍ መቃብር ነዉ ብለዉ የሚያከብሩትን ይህን ስፍራ ሙስሊሞች በበኩላቸዉ ከሁለት ምዕተ ዓመታት በፊት ሼይክ ዩሱፍ የተቀበሩበት ነዉ እንደሚሉ ተገልጿል። ስፍራዉ በእሳት የተለኮሰዉ ፍልስጤሞች ዛሬ በእስራኤል ላይ አብዮት ለማካሄድ በሚል የተቃዉሞ ሰልፍ በጠሩበት ዋዜማ ነዉ። የኢየሩሳሌም ፖሊስ የወጣት ፍልስጤማዉያንን የተቃዉሞ እንቅስቃሴ ለማስቆም በአላቅሳ መስጊድ በሚካሄደዉ የዓርብ ፀሎት ላይ እድሜያቸዉ ከ40 ዓመት በታች የሆኑት እንዳይሳተፉ አግዷል። በርካታ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎችም ኢየሩሳሌም ዉስጥ ተሰማርተዋል። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፍልስጤም ፕሬዝደንት አባስ ጋር ተገናኝተዉ እንደሚነጋገሩ ያስታወቁ ሲሆን ሀገራቸዉ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል የትኛዉም ሀገር የሚወስደዉን ሕጋዊ ርምጃ እየወሰደች እንደሆነም አስታዉቀዋል።
«እስራኤል የየትኛዉም መንግሥት የከተማ አስተዳደሮች እና የፖሊስ ኃይሎች ቢላዎችና የሥጋ መቁረጫዎች፣ መጥረቢያ እና የመሳሰሉትን በመያዝ ሰዎችን ለመግደል በሚሞክሩ ላይ የሚወስደዉ ዓይነትና ሕጋዊ ርምጃ እየወሰደች ነዉ።»

ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic